በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የተሽከርካሪዎች ባሉበት ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/የግ/ማ የተለያዩ አይነት ያገለገሉ የተሽከርካሪዎች ከታች በዝርዝር የቀረቡትን ባሉበት ቦታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የመኪናው ዓይነት |
መኪናው የተሰራበት ዘመን እ.ኤ.አ |
መኪናው የተሰራበት ሀገር |
የጭነት መጠን |
የሞተር ችሎታ (ሲሲ) |
ተሽከርካሪው የሚገኝበት ቦታ |
|
1 |
ኒሳን ፓትሮል / Nissan Patrol/ |
2011 |
ጃፓን |
6 ሰው |
5552 |
ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ |
|
2 |
ፋኦ አውቶሞቪል /FAW Automobile/ |
2012 |
ቻይና |
4 ሰው |
1290 |
ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ |
|
3 |
ታታ ፒክ አፕ (TATA XENON) |
2013 |
ህንድ |
1 ሰውና 10 ኩንታል |
2200 |
ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ |
1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናቶች በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ በመቅረብ ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ የሚያስገቡትን ዋጋ መጠን 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ተሞልቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች መኪኖቹን ባሉበት ቦታ በድርጅቱ የስራ ሰዓት በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀን እና የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 16ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ለቡ ኢንዱስትሪ መንደር በአካል በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው በደብዳቤ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን አጠቃላይ ዋጋ ከፍሎ ተሽከርካሪውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ የሚወረስ ይሆናል።
6. ለተሽከርካሪ የስም ማዛወሪያና ተያያዥ ሌሎች ወጭዎች እና ከቦታ ለማንሳት የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ወጪዎች ሙሉ በሙሉ በገዥ የሚሸፈን ይሆናል።
7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 39 55 46 06 / 09 12 50 32 75 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ።
በላይአብ ኬብል አምራች ኃ/የተ/ግ/ማ
Tender details
- Deadline: 2026-04-23
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-23 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Belayab Cables Manufacturing P.L.C.
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Apr 05, 2026
- Posted at: 2026-04-06T12:07:50.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.