በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ለ2018 በጀት አመት መገልገያ የሚውሉ ሎት 1፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፤ ሎት7 የህክምና እቃ፣ሎት 3, ህትመት፣ ሎት 2, የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 5, ጥገና እቃዎች፣ ሎት 6, ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 4, መድሃኒቶች፣ ሎት 8 ልብስ ስፌት፤ ሎት 9 የኤሌትሮኒክስ እቃዎች ጥገና መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቹሁ በተሰማሩበት የስራ መስክ የንግድ ፈቃድን፣ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (vat) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሽያጭ በየሎቱ 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ነው።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት የሚያገለግል የመጫረቻ ዋጋ 5000.00 / አምስት ሺህ ብር/ ብቻ በድርጅቱ ስም ሲፒኦ በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ሞልተው በመፈራረም እና የደርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 41 ረዳት ፋይናንስ በመገኘት ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
8. የጨረታው ሳጥን የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው(አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ጠዋት 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት በወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ የግ/ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 46 ጨረታው በግልጽ ይከፈታል፤
9. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ሰርዞ ጎኑ ላይ ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል።
11. አሸናፊው ድርጀት ማሸናፉ ከተገለፀበት በ7 ቀናት ውስጥ የመደበኛ ውል ሰነድ መፈራረም ይኖርበታል።
12. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ገደራ ሳራ አምፖል አካባቢ
በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የህዳሴ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-04-17
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው(አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-17 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው(አስራ አንደኛው) የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Hidase Health Post
- Buyer address: ህዳሴ ጤና ጣቢያ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ገደራ ሳራ አምፖል አካባቢ
- Bid bond: 5,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 200.00 ብር በየሎቱ
- Published: Apr 05, 2026
- Posted at: 2026-04-06T12:13:26.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.