ፀደይ ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ሁለት ሚድ ባሶች እና አንድ ቮልስ ዋገን አዉቶሞቲቭ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ፀደይ ባንክ/አ.ማ/ Tsedey Bank (S.C)

በድጋሚ የወጣ የሽያጭ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ብ/ግ/ጨ/003/2018

ፀደይ ባንክ አማ ያገለገሉ ሁለተ ሚድ ባሶች እና አንድ ቮልስ ዋገን አዉቶ ሞቲቭ መኪኖችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተሸከርካሪው አይነት

ብዛት

ሞዴል

የምርት ዘመን

የመጫን አቅም

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

1

አነስተኛ አውቶብስ

2

Daewoo

2013 GC

22 ሰው

ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት

2

አውቶሞቢል

1

Volkswagen SURAN

2008 GC

4 ሰው

ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ የሚያሟላ ማንኛውም ፍላጎት ያለው ግለሰብ /ድርጅት/ መወዳደር የሚችል መሆኑን እንገልጻለን።

1. በጨረታው በሁሉም አይነት ወይም በከፊል መወዳደር ይቻላል

2. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው የመኪና አይነቶች የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው የዋጋ ፎርማት ላይ መሙላት ይኖርባቸዋል። በነጠላ ዋጋና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው የሚያዝ ይሆናል። ዋጋ ሲሞላ ስርዝ ካለ ፊርማ ሊኖረው ይገባል። ሆኖም ግን ስርዝ ድልዝ ከበዛበትና ግልፀኝነት ከጐደለው ተወዳዳሪው ከጨረታው ይሰረዛል።

3. ለጨረታ ማስከበሪያ የአጠቃላይ ዋጋውን 2% በሲፒኦ /CPO/ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የ 90 ቀን በፀደይ ባንክ አማ ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል። ከየትኛውም የፀደይ ባንክ አማ ቅርንጫፍ የተሰጠ ሲፒኦም ሆነ ባንክ ጋራንቲ ተቀባይነት የለውም።

4. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከመጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት የስራ ቀኖች ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ 6:00 ሰዓት የማይመለስ ሁለት መቶ ብር /200.00/ ፀደይ ባንክ ለገሃር ቅርንጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል ሰንጋተራ አካባቢ ጤና ሚኒስቴር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ከግዥ ክፍል ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ ሚያዚያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ ስንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት 16ተኛ ፎቅ ግዥና ዉል አስተዳደር ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

6. የጨረታዉ መዝጊያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ ማንኛዉም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረዉም።

7. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 011 558 1658

ፀደይ ባንክ አ.ማ.


Tender details

  • Deadline: 2026-04-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-04-28 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Tsedey Bank S.C.
  • Buyer address: Legahar Orda Building, 8th Floor room No-804
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T13:34:14.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders