ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ልዩ ልዩ መድኃኒቶችን እና ሕክምና መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

"Tender care for women with childbirth injuries"

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን የአዋላጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፤ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዞን በሚገኛው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፡ በምንሰጠው ሕክምና ለዳኑና ተጨማሪ የቅርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ከላይ የተገለፁትን አገልግሎቶች መስጠት እንዲችል፣ልዩ ልዩ መድኃኒቶችን እና ሕክምና መገልገያዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ጨረታው ከመጋቢት 27፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዕረቡ ሚያዚያ 7፣ 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

ተወዳዳሪ ድርጅቶች ዝርዝር የጨረታውን መመሪያ፣ እንዲሁም ግዢ የሚፈፀምባቸውን መድኃኒቶቸችና የሕክምና መገልገያዎች አይነትና ብዛት የሚገልፀውን ሰነድ፡ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የፋይናንስና ግዢ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ይህንን ጨረታ በከፊል ወይንም ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ተወዳዳሪ ድርጅቶች ጨረታውን በተመለከተ ለሚያስፈልጋቸው ማናቸውም ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-371-6544/45/46-የውስጥ መስመር 125/198/199 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-13
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ከመጋቢት 27፣ 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-04-15 14:30
  • Bid opening (note): ሚያዚያ 7፣ 2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hamlin Fistula Ethiopia
  • Buyer address: Kolfe Keranyo Sub city woreda 09, House number 920 Betel Hospital Street behind Augusta Shirt Factory
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 05, 2026
  • Posted at: 2026-04-06T13:54:04.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders