የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ለቢሮ እና ለገቢ ማስገኛ እየተጠቀመባቸው የሚገኙ ህንፃዎችን ማለትም አዲስ አበባ (የቦሌ ባለ አራት ወለል ህንፃ እና አራት ኪሎ ባለ አራት ወለል ህንፃ)፣ ባሕር ዳር ባለ አራት ወለል ህንፃ፣ ደሴ ባለአራት ወለል ህንፃ፣ ደብረ ብርሃን ባለ አራት ወለል ህንፃ እና ጎንደር ባለ አንድ ወለል ህንፃ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች ለ2ተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር

Description

ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

አማራ ልማት ማህበር (አልማ) የክልሉን ህዝብና ልማት ደጋፊዎችን በዘላቂነት የማንቀሳቀስ በትምህርት፣ በጤና እና በስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ ለክልሉ ህዝብ የማህበራዊ ልማት ተጠቃሚነት አስተዋፅኦ የማድረግ ተልዕኮ አንግቦ በመስራት ላይ የሚገኝ መንግስታዊ ያልሆነ ሀገር በቀል የልማት ማህበር ነው፡፡ ማህበሩ ለቢሮ እና ለገቢ ማስገኛ እየተጠቀመባቸው የሚገኙ ህንፃዎችን ማለትም አዲስ አበባ (የቦሌ ባለ አራት ወለል ህንፃ እና አራት ኪሎ ባለ አራት ወለል ህንፃ)፣ ባሕር ዳር ባለ አራት ወለል ህንፃ፣ ደሴ ባለአራት ወለል ህንፃ፣ ደብረ ብርሃን ባለ አራት ወለል ህንፃ እና ጎንደር ባለ አንድ ወለል ህንፃ በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ድርጅቶች ለ2ተኛ ጊዜ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር As Built Design እና የህንፃ ግምታዊ ዋጋ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ብቻ በመክፈል ባሕር ዳር በሚገኘው አልማ ዋናው መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 108 ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች በማህበሩ የተዘጋጀውን የፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ በትክክል በመሙላት ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነዱን ለየብቻ በኢንቨሎፕ በማሸግ በግልጽ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስገባት አለባቸው፡፡

7. ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች መሠረት በማድረግ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነዶችን ለመለየት እንዲቻል በግልጽ ፁሁፍ ኢንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ዋናው መ/ቤት ባሕር ዳር ቢሮ ቁጥር G-03 ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ይታሸጋል፡፡ በእለቱ በ9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር G-03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 320 73 60 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአማራ ልማት ማህበር (አልማ)


Tender details

  • Deadline: 2026-04-16
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30
  • Bid opening: 2026-04-16 15:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ በ9፡00
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Development Association (ADA)
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published: Apr 06, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T07:50:38.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders