ቫላም ግሎባል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ የኤክስፖርት የእህል ማበጠሪያ እና ማቀነባበሪያ ማሽነሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የኤክስፖርት እህል ማቀነባበሪያ

ማሽን ሽያጭ ጨረታ

ድርጅታችን ቫላም ግሎባል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ ቱርክ ሰራሽ የእህል ማበጠሪያ እና ማቀነባበሪያ ማሽነሪዎች ማለትም፤ ቅድመ ማበጠሪያ ማሽን፤ ዲስቶነር (ድንጋያማ ቆሻሻ መለያ)፤ ግራቪቲ መለያ ማሽን፤ የተበጠረ ማጠረቀሚያ ቋቶችና የመስፊያ ማሽን፤ የተለያዩ ለማሽኑ የሚያስፈለጉ መሳሪያዎች....የመሳሰሉትን በአሉበት ሁኔታ ድርጅታችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ማሽኖቹን ለመግዛት የሚፈልግ ተጫራች በጽሁፍ የተዘጋጀውን ዝርዝር የማሽን ዓይነት በመውሰድ ማሽኖቹን በመመልከትና የመግዣ ዋጋ (ተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት) በታሸገ እንቨሎፕ ከአስር በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርብታል።

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል። በአስራ ስድስተኛው እለት ጨረታው ተዘግቶ በእለቱ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በአራት ሰዓት ይከፈታል። አስራ ስድስተኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ላይ ይከፈታል።

የጨረታውን ዶክመንት ለመውሰድና ማሽኖቹን ለማየት በሞባይል ቁጥር 0930 175 834 እና 0910 314 271 ላይ በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ቫላም ግሎባል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው እለት
  • Bid opening: 2026-04-21 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው እለት ከጠዋቱ በአራት ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Valam Global Trading Plc
  • Bid bond: 10%
  • Published: Apr 06, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T08:09:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders