የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ግማሽ ሊትር የታሸገ ውኃ እና የተለያዩ ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

በድጋሜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ 003/2018

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮው የሚያስፈልጉ የተለያዩ እቃዎች

  • ሎት 1፡-ግማሽ ሊትር የታሸገ ንፁህ ውኃ፤
  • ሎት 2፡ የተለያዩ ህትመቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድና ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ አለባቸው፡፡በኢፌዴሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡበት ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው።

2. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 400/ አራት መቶ ብር/ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ በሚገኘው የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ህንፃ (ዋስትና የንግድ ማዕከል)18ኛ ፎቅ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ህጋዊ ሥልጣን (ባለቤት) ያለው አካል ፊርማና ማህተም በማኖር በሰም በታሸገ ማህተም ያረፈበት ኤንቨሎኘ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ከረፋዱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፒያሳ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ህንፃ (ዋስትና የንግድ ማዕከል) 18ኛ ፎቅ የግዥ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11 ኛው ቀን በዓል ፣ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል።

5. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡እያንዳንዱ ተወዳዳሪ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

6. በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

7. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነበትን እቃዎች በወቅቱ በተገቢው የማስረከብ ግዴታ አለባቸው።

8. ተወዳዳሪ ንግድ ድርጅቶች ሁሉንም ሎቶች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በውላቸው መሠረት በወቅቱ በሚሰጡ ትዕዛዞች ማቅረብ አለባቸው፡፡ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ ቀርበው ውል መዋዋል አለባቸው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0111262185
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-18
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት
  • Bid opening: 2026-04-18 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሠዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Labor, Enterprise and Industry Development Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published: Apr 07, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T08:38:43.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders