በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤት ሠራተኞች የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

 ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፣

  • የታደሰ የዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
  • የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  • የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ያለው፣ 
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

ከላይ በዝርዝር የተቀመጠውን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የደንብ ልብስ የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፣ ቫትን ያላከተተ ከሆነ ቫትን እንዳካተተ ተደርጎ ይቆጠራል።
  • ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ብር 60,000 /ስልሳ ሺህ ብር/ ሲፒኦ እና ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም በባንክ ዋስትና ሆኖ በጥሬ ገንዘብ ብቻ ዋስትና ማቅረብ አይቻልም።
  • ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በተዘጋጀው ዝርዝር ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልተው አንድ ኦርጅናል ሰነድ እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ፖስታ ካሸጉ በኋላ ከሲፒኦ ጋር በአንድ ትልቅ ፖስታ በሰም በማሸግ ማቅረብ ይገባቸዋል።
  • ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ላይ ማንኛውም አይነት ስርዝ ድልዝ /በፍሉድ የተስተካከለ በሚታይ መልኩ በድጋሚ ተጽፎ በተጫራች ወይም በሕጋዊ ተወካይ መፈረም አለበት።
  • በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ሕጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማረፍ አለበት፣
  • ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ወጥቶ በአየር ላይ ከዋለበት በተከታታይ በሚቆጠር 21 ቀናት በኋላ በ22ኛው ቀን ጠዋት የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች በዕለቱ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ሠዓት ባለው ጊዜ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
  • የጨረታው ሳጥን የሚገኘው በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ቅጥር ግቢ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ነው።
  • ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የደንብ ልብስ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች በጨረታው ተወዳድረው ያሸነፉትን የደንብ ልብስ ጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማጓጓዣ፣ የማስጫኛ እና የማውረጃ ወጪ ችለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን በኋላ ለ 2 ወር ማለትም ለ60 ቀናት ጸንቶ ይታያል።
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046 131 0108 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-28 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: በጌዴኦ ዞን ፋይናንስና ፕላን መምሪያ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
  • Bid bond: 60,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 07, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T08:57:47.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders