Uniforms and workwear
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ፤ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች የ2019 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ ግዥ ለመፈፀም፤ በዘርፉ የተሰማሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ሊያሟሉ የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ (ታክስ ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ፤
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
4. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፤
5. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ፣ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ፧ ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /ለአስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርበው ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በከተማ አስተዳደሩ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በመክፈል ሰነድ መግዛት እና ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት።
8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (ለአስር) ተከታታይ ቀናት በፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም )፤ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት በዕለቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል። ይህ ቀን የበዓል ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ፤ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ ረታውን መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 046-212-1334
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-19
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-19 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Administration Finance & Economic Development Bureau
- Bid bond: 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T08:04:26.000Z