Uniforms and workwear
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ በ2019 ዓ/ም ለክለቡ ስፓርተኞችና ኮች ስታፍ የስፖርት ትጥቅ ግዢ ለመፈፀም በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ላይ ከተማ ስፖርት ክለብ በ2019 ዓ/ም ለክለቡ ስፓርተኞችና ኮች ስታፍ የስፖርት ትጥቅ ግዢ ለመፈፀም በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት፤-
ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ።
- በሥራ መስኩ ሕጋዊ የታደሠ ንግድ ፍቃድ፤የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለተመዘገቡ ጨረታዎች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ (የምስክር) ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቀረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ ስፖርት ከለብ ቢሮ በመቀረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም ብር 3,000.00/ ሶስት ሺህ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሠነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በማያያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ ቀናትን በመጠቀም በሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ ፋይናንስ ቢሮ አርተፍሻል ሜዳ ቢሮ ቁጥር 1 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ ሰነድ ላይ ለሚጠየቁ ዕቃዎች ናሙና የጨረታው ሠነድ በሚገባ ቀን ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ላይ ኮድ የድርጅቱን ማህተም/ በማስቀመጥ በጨረታው አከፋፈት ሥነሥርዓት ላይ መቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ እሁድ ከሆነ እንዲሁም የበዓላት ቀን ከሆነ በተመሣሣይ ሰዓት በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ ተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡-046-212-4176
የሀዋሳ ከተማ ስፖርት ክለብ
Tender details
- Deadline: 2026-08-22
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-22 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Hawassa City Sport Club
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 3,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 07, 2026)
- Posted at: 2026-08-07T08:36:37.000Z