Uniforms and workwear

በጉ/ከ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር የደንብ ልብስ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የተለያዩ የተገጣጣሚ፤ህንፃ ጥገና እቃዎች፣ የመኪና እቃዎች፣ የተለያዩ መገልጊያ መሳሪያዎች እና ቋሚ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

በጉ/ከ/ከ/ፐ/ሰ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ለ2019 በጀት ዓመት በፑሉ ስር ለሚገኙ ጽ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችና አልግሎቶች በአጠቃላይ 8 ሎቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ ዕቃዎች
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት 3 የፅህፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 4 የፅዳት እቃዎች
  • ሎት 5 የተለያዩ የተገጣጣሚ፤ህንፃ ጥገና እቃዎች
  • ሎት 6 የመኪና እቃዎች
  • ሎት 7 የተለያዩ መገልጊያ መሳሪያዎች
  • ሎት 8 ቋሚ እቃዎች
  1. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ጨረታ ፖስታ ላይ ለየትኛው አገልግሎት እንደሚወዳደሩ በግልፅ ለይተው መጻፍ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ድረ ገፅ (ዌብ ሳይት) ላይ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ክሊራንስ ማቅረብ እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም አስተዳደሩ ባወጣው ጨረታ ላይ ከውል በፊት የዕቃውን ብዛት 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል እንዲሁም ከውል በኃላ ደግሞ 25% የዋጋውን መጨመር ይችላል።
  4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል እንዲሁም ተጫራቾች ለተወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ማስገባት አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው አገልግሎቶች ወይም ዕቃዎች በሙሉ መስሪያ ቤቱ ቴክኒክ ኮሚቴ ደረጃቸውን የጠበቁ ስለመሆናቸው ይገመግማሉ።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆኑን ወይም ዋጋው ከቫት ውጪ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው ይህ ባይሆን ዋጋው ቫት ያካተተ ተደርጐ ይወሰዳል።
  7. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች አሸናፊ ሆኖ በደብዳቤ ካወቀ ጀምሮ የቅሬታ ሰባት ቀን ካለፈ በኃላ ውል ተዋውሎ እቃዎችን በአምስት የስራ ቀናት ውስጥ ወደ ስቶር ገቢ ለማድረግ መስማማት አለበት።
  8. ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ ሎት 1 10,000/አስር ሺህ ብር/ ሎት 2 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ሎት 3 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ሎት 4 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር/ ሎት 5 10,000/አስር ሺህ ብር/ እና ሎት 6 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ሎት 7 15,000/አስራ አምስት ሺህ ብር እና ሎት 8 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/ የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት ክ/ሂ ቡድን ስም በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት ወይም ስነድ በመክፈል በመንግስት የስራ ሰዓት ጉለሌ ከፍለ ከተማ ፐ/የሰ/ሀ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን ቢሮ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
  10. የጨረታ ሰነዶች በሙሉ በኢንቨሎፕ ታሽገው ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለየብቻው በማድረግና በማያያዝ ማህተማቸውን በፖስታዎች ላይ በማኖር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  11. የካፒታል መጠናቸው ከብር 100,000 /አንድ መቶ ሺ ብር/ በላይ የሆኑ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  12. የጨረታው ጊዜ የሚያበቃው በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጐ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ይሆናል።
  13. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ ባቀረቡት የመወዳደሪያ ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው እራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
  14. በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየተጋበዙ እንዲሁም ከአደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ በነፃ እንዲወስዱ፤በጨረታ ማስከበሪያ እና በውል ማስከበሪያነት የሚያገለግል በግልፅና በዝርዝር በተፃፈ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው።
  15. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው የሚሰረዙ ይሆናል።
  16. አንድ ተጫራች ሌላው ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  17. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በገዙት ጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ይህ ባይሆን ግን ከጨረታ ይሰረዛሉ።
  18. ተጫራቾች በንግድ ፍቃዳቸው በስተጀርባ ላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ዘርፍ አይነቶች ኮፒ አድርገው ማቅረብ አለባቸው የተጫራቾች ማህተምና የንግድ ፈቃዳቸው እንዲሁም የደረሰኛቸው ስያሜ አንድ አይነት መሆን ይኖርበታል።
  19. በጨረታ መወዳደሪያ የሚቀርብ ዋጋ ለስድስት ወር ፀንቶ ይቆያል
  20. ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ማስከበሪያ ላሸነፉባቸው አገልግሎት ወይም ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋውን 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ግን በጨረታ ያስያዙት /ሲፒኦ/ በቀጥታ ለመንግስት ገቢ ሆኖ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
  21. ተጫራች አሸነፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ወጪ መ/ቤታችን ወይም በሚፈለግበት ቦታ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
  22. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 812 5178 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።

በጉ/ክ/ከ/ፐ/ሰ/የሰው /ኃ/ል/ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ አስተዳደር ቡድን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-19
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-20 09:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጐ በሚቀጥለው የስራ ቀን 3:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Public Service and Human Resource Development Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 08, 2026)
  • Posted at: 2026-08-08T08:33:51.000Z
← Back to all tenders