በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ድ/ ዳ/ ድ/ ጮ/ ሆ/09/18
በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም ለሆስፒታሉ ያገለገሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
1. አንድ ተጫራች ጨረታ ሰነድ በሚገዛበት ጊዜ የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ አቅርቦ ሰነድ መግዛት ይችላል፡፡
2. የሽያጭ ፈጻሚው አካል በወጣው ጨረታ ምክንያት የተቀበላቸውን ከተጫራቾች የሚቀርቡ የመጫረቻ ሰነዶች በባለቤትነት የመያዘ መብቱ የተጠበቀ ነው። በመሆኑም ዘግይተው የደረሱ ጨረታዎች ካልሆኑ በስተቀር ተጫራቾች ያቀረቡት የመጫረቻ ሰነድ እንዲመለስላቸው የመጠየቅ መብት አይኖራቸውም፡፡
3. አንድ ተጫራች ጨረታ በሚያቀርብበት ጊዜ በጨረታ ሰነዱን የተመለከቱትን የሽያጭ ሥነ ስርዓቶችና ሁኔታዎች ያለምንም ገደብ እንደተቀበለ ይቆጠራል። ስለሆነም ተጫራቾች ጨረታ ከማቅረባቸው በፊት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ዝርዝር መስፈርቶች በጥንቃቄ ሊመረምራቸው ይገባል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100000 /አንድ ሺ ብር/ ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል በድል ጮራ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር A/02 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
5. መስፈርቱን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር CPO እና በጥሬ ብር ብቻ ነው
- ሎት 01- ብረታ ብረቶች CPO 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ሎት 02- የህክምና መ/መሣ CPO 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/
- ሎት 03- ወረቀቶች CPO 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ ብር/
- ሎት 04- የፍሪጆች CPO 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/
- ሎት 05 - የመኪና ዕቃዎች CPO 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/
- ሎት 06- TV computer and Electronics CPO 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ ጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. የጨረታ ሰነዱን የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ የግዢ/ፋ/ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 155 ይከፈታል፡፡
8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሑፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈራረም አለበት። ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
9. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ሙሉ አድራሻቸው እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም፡፡
11. አንድ ተጫራች አንድ መደብ ወይም ከአንድ በላይ መደብ /በመለያ ቁጥሮች የተጠቀሱትን ልዩ ልዩ ሎቶች ዕቃዎችን መጫረት ይችላል፡፡
12. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ 05/ አምስት የስራ ቀኖች ውስጥ/ እቃዎቹን ማንሳት ይኖርበታል። በተጠቀሰው ቀን ካላነሱ በየቀኑ 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ታስቦ ለሆስፒታሉ ይከፍላል፡፡
13. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰብ ጨረታው አንድ ሎት ሲያሸነፍ በስሩ የተጠቀሰውን ኪሎግራም ብዛት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተጠቀሰውን መጠን ብቻ ሳይሆን የቀረበውን መጠን በሙሉ ባሸነፈበት ዋጋ
14. ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ስልክ ቁጥር 0982540408/0901103211/2-521115693
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 177
በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-04-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00
- Bid opening: 2026-04-24 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡30
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: ድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታል
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/ ለእያንዳንዱ
- Published: Apr 07, 2026
- Posted at: 2026-04-07T09:11:17.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.