ወላይታ ልማት ማህበር ማህበሩን ለማጠናከር በመካሄድ ላይ በሚገኘው ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በወላይታ ዞን (ወላይታ ሶዶ፣ አረካ፣ ጠበላ፣ በሌ አዋሳ፣ ዲምቱ፣ ዳንጋራ ሰላጣ፣ አፋማ ጋሮ፣ ሄምቤቾ፣ ሃላሌ፣ ጎጮ እና ላሾ) ከተሞች የሚገኙ ለንግድና መኖሪያ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ወላይታ ልማት ማህበር የቤት ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ወልማ 001/2026
ወላይታ ልማት ማህበር ማህበሩን ለማጠናከር በመካሄድ ላይ በሚገኘው ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በወላይታ ዞን (ወላይታ ሶዶ፣አረካ፣ ጠበላ፣ በሌ አዋሳ፣ ዲምቱ፣ ዳንጋራ ሰላጣ፣አፋማ ጋሮ፣ ሄምቤቾ፣ ሃላሌ፣ ጎጮ እና ላሾ) ከተሞች የሚገኙ ለንግድና መኖሪያ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. በጨረታ የሚሳተፉ ግለሰቦች ከሆኑ ህጋዊ መታወቂያ፣ ድርጅቶች ከሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ህጋዊ የመታወቂያ ካርድ ህጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሠነድ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15ኛው በማህበሩ የሥራ ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን ወላይታ ሶዶ ከሚገኘው ወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል፣ በወላይታ ልማት ማህበር አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ሰሜን ሆቴል ፊት ለፊት ዳትሰን ሠፈር 100 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው ቢሮ እንዲሁም ሀዋሳ፣ ሻሸመኔ፣ ዲላ ከተሞች በሚገኙ የወላይታ ልማት ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10% ለቤቱ ሽያጭ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋ መሰረት በማናቸውም ንግድ ባንኮች የተመሰከረለት በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሠራውን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር አያይዘው በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ቤት ኮድ በመምረጥ የጨረታ ሰነድና ዋጋ ማቅረቢያውን ሳይዘለል፤ ሳይታለፍ ስርዝ ድልዝ ሳይገኝበት በሙሉ አጠናቅቆ በመሙላት ዋናውንና አንድ ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማሸግ ወላይታ ሶዶ በሚገኘው የወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በሚቆጠር በማህበሩ ሥራ ቀንና ሰዓት እስከ 15ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀ ጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥን በዕለቱ ልክ በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ /ታሸጎ/ ፈቃደኛ የሆነ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ በ9፡30 ሰዓት ወላይታ ሶዶ በሚገኘው የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት በይፋ ይከፈታል። 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ሕጋዊ በዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
5. የጨረታው ሂደት የሚከናወነው ተጫራቹ መግዛት ለሚፈልገው ቤት ያቀረበውን ጠቅላላ ዋጋ መሰረት በማድረግ ይሆናል።
6. አሸናፊ ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመቅረብ ውል መግባት የሚኖርበት ሲሆን ይህን ካልፈጸመ ጨረታውን በፈቃዱ እንደሰረዘ ተቆጥሮ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
7. ተጫራቹ በጨረታው ማሸነፉን በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጨረታ ያሸነፈበትን ቤት ዋጋ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት ገንዘቡን በማህበሩ አካውንት ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
8. በጨረታ ያሸነፉትን ቤቶች ውል ለማጸደቅ፣ ስም ለማዛወርና ማናቸውንም ተያያዥ ወጪዎች ገዥው ይሸፍናል።
9. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ቤቶቹ በሚገኙበት ከተማ ማህበሩ በሚያመቻቸው ሰዓት ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
10. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
11. የጨረታ ሠነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም።
12. ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይፈቀድም።
13. ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ወላይታ ሶዶ 0910 54 19 63 / 0913 255 729
አዲስ አበባ 0916 833 499፣ ሀዋሳ 0916 834 480፤
ሻሸመኔ 0916 870 242፣ ዲላ 0912 607 054
ወላይታ ልማት ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-04-23
- Bid closing time: 15:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-23 15:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ሥራ ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Wolaita Development Association
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 07, 2026
- Posted at: 2026-04-07T09:36:19.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.