Property and building sale
ኢቲሲኤል ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አካባቢ የሚገኘው እና አገልግሎቱ ለመኖሪያ አፓርትመንት የሆነው ብሎክ ላይ የሚገኙ የአፓርትመንት ቤቶችን በከፊል በተጠናቀቀ ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
2ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ ሜክሲኮ አካባቢ የሚገኘው እና አገልግሎቱ ለመኖሪያ አፓርትመንት የሆነው ብሎክ ላይ የሚገኙ የአፓርትመንት ቤቶችን በከፊል በተጠናቀቀ ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። የቤቶቹ መነሻ ዋጋ 89,000 ብር በካሬ ነው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ኦሪጅናልና ኮፒ፣ በውክልና ሰነድ ለመግዛት ከፈለጉ የውክልና ማስረጃ እና መታወቂያ ይዞ በአካል መቅረብ ይኖርበታል።
- በኢቲሲኤል ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኝው የአፓርትመንት ህንፃ ላይ በመምጣት የቋሚ ንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በብር 1,000.00 (አንድ ሺ) ብቻ ከፍለዉ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚገዙት/የሚገዟቸው ንብረቶች 100,000.00(አንድ መቶ ሺ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ለኢቲሲኤል ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህ (ETCl Real Estate PLC) እንዲከፈል የታዘዘ ሲፒኦ CPO ከጨረታ ሰነዱ ጋር እና ማንነቱን የሚገልፅ መታወቂያ ኮፒ በማያያዝ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ንብረቶች 30% በአስር ቀናት ውስጥ የሚከፍሉ ሲሆን ቀሪውን 70% ደግሞ በሚቀጥሉት 12 ወራት ውስጥ የሚከፍሉ ይሆናል።
- ተጫራች የጨረታ ሰነድ ገዝተው ማስታወቂው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት በስራ ሰዓት ውስጥ በመገኘት ለጨረታ የቀረቡትን ቋሚ ንብረቶች መመልከት ይችላሉ።
- የጨረታ ሳጥኑ ነሃሴ 18/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል። የአሸናፊዋችም ስም ዝርዝር በቀጣዩ እለት በድርጅቱ ቢሮ ይለጠፋል።
- አጫራች በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-557-5049 ወይም 011-126-6120 ወይም 09-77-55 50-27 ይደውሉ።
ኢቲሲኤል ሪል እስቴት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ነሃሴ 18/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00
- Bid opening: 2026-08-25 16:00
- Bid opening (note): ነሃሴ 18/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ETCL REAL ESTATE PLC
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jul 29, 2026)
- Posted at: 2026-07-29T09:44:43.000Z