የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አ/ማ ከሰኔ 30 2018 ዓ.ም የሂሳብ ዘመን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ዓመት የሚቆይ የኦዲት አገልግሎት ግዥ ለማከናወን ብቁ የኦዲት ድርጅቶችን እንዲሁም አክሲዮኖችን በካፒታል ገበያ ባላስልጣን ለማስመዝገብ ከተቀጠረው የግብይት አማካሪ ጋር ተናቦ የሚሰራ የህግ ምክር አገልግሎት ግዥ ብቁ ከሆኑ የህግ አገልግሎት ድርጅቶች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የውጭ ኦዲት አገልግሎት ግዥ እና የሕግ

አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አ/ማ ከሰኔ 30 2018 ዓ.ም የሂሳብ ዘመን ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ዓመት የሚቆይ የኦዲት አገልግሎት ግዥ ለማከናዎን ብቁ የኦዲት ድርጅቶችን እንዲሁም አክሲዮኖችን በካፒታል ገበያ ባላስልጣን ለማስመዝገብ ከተቀጠረው የግብይት አማካሪ ጋር ተናቦ የሚሰራ የህግ ምክር አገልግሎት ግዥ ብቁ ከሆኑ የህግ አገልግሎት ድርጅቶች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

በመሆኑም

1. የታደሠ የንግድ ፈቃድና በየሙያ ዘርፋቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ

2. የዘመኑ የንግድ ግብር ክፍያ የተፈጸመ መሆኑን የሚያስረዳ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማረጋገጫ

3. ለተጨማ እሴት ታክስ እና ለግብር ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያስረዳ የምዘገባ ሰርትፍኬት ማቅረብ

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመተፍ ከላይ ከተቁ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚዘጋበት ቀን ድረስ አዲስ አበባ 4ኪሎ አካባቢ በሚገኘው ጽ/ቤታችን አልማ (አሚኮ) ህንፃ ግዥ ክፍል የማይመለስ ብር 200-- በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን በመሙላት ማህተምና ፊርማ በመጨመር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለድርጅቱ መመለስ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በአቅራቢው ስም ለግዥ ፈፃሚ መ/ቤት ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

8. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ ማስታወቂያው በአየር ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፣

9. የጨረታ ሰነድ ፀንቶ መቆያ ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት እለት ጀምሮ ለ20 ቀናት ይሆናል።

10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር ስልክ: 0920 874432/0918 700707

ኢሜይል: info@abayindustrial.com  መጠየቅ ይችላሉ።

ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-04-22
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00
  • Bid opening: 2026-04-22 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሆኖ ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Abay Industrial Development Share Company
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 07, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T09:46:06.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders