በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን ዱራሜ ዲስትሪክት ጽህፈት ቤት የደንብ ልብስ መግዛት ይፈልጋል

Description

የደንብ ልብስ ጨረታ

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ በመስኩ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ስለሚገዛው የሥራ ልብስ በቀረበው ስፔስፍኬሽን መሠረት ልብሱ የተሠራበትን ጨርቅ የተመረተበትን ፋብሪካ፣ የተሠራበት የጥጥና የሴንቲቲክ መጠን ወዘተ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን ዓይነት ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ በሚያቀርቡት ናሙና ላይ ሞዴሉ ወይም የጨርቁን ዓይነት የሚገልጽ በጨረታ ሰነዱ ላይ ካለው ጋር ማገናዘብ በሚችል መልኩ በዕቃዎቹ ላይ ጽፎ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚቀርበው የጨርቅ ናሙና ከ5 ሳንቲ ሜትር ያላነሰ መሆን አለበት።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ5 ቀናት ከዱራሜ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን 15ኛው ቀን 11፡30 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡00 ሰአት ይታሸግና 3፡15 ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል ሆኖም የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታ ሰነዱን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በሰም የታሸገ ፖስታ ሆኖ ፖስታው ላይ የድርጅታቸውን ስም፣ አድራሻና የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት በመለየት ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው ዝርዝር መሠረት በትክክል ማስፈር አለባቸው።

6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይችሉም።

7. አሸናፊውን ተጫራች ለመምረጥ የሚከተሉትን ዘዴዎች መሠረት በማድረግ ተጫራቾች ያቀረቧቸው የጨረታ ሰነዶች ይገመገማሉ።

ሀ. የመወዳደሪያ ዋጋ …80%

ለ. የዕቃው ጥራት..20%

8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ከተገለፀበት 5(አምስት) ቀናት ውስጥ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና (ፐሮፎርማንስ ቦንድ 10% የባንክ ጋራንቲ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ሲ.ፒ.ኦ) በማቅረብ ውል መፈራረም አለበት።

9. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ የሚሰጡት ዋጋ የሚጫረቱበትን የዕቃ ዋጋ ብቻ ይሆናል በመሆኑም የማጓጓዣና ሌሎች ማናቸውንም ወጪዎች አያካትትም።

10. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ያቀረቡት ዋጋ ቢያንስ ለ60 (ስልሣ) ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።

11. ባለሥልጣኑ መ/ቤት ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ +251911973776/+251926545089

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንገዶች ባለሥልጣን

ዱራሜ ዲስትሪክት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-21
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡00 ሰአት
  • Bid opening: 2026-04-21 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ16ኛው ቀን 3፡15 ሰአት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: Central Ethiopia Roads Authority Durame District Bureau
  • Published: Apr 06, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T10:09:15.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders