የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የግንባታ ስራዎች ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በአለታ ጩኮ ወረዳ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት ሊያሰራ ላቀደው እና ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተዘረዘሩትን የግንባታ ስራዎች ህጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በአለታ ጩኮ ወረዳ ማሰራት ይፈልጋል።

/

የግንባታ ሥራው ዓይነት

ግንባታው የሚሠራበትቦት

ሎት

የጨረታ ማስከበርያ

1

በቁፋሮ ማሸን (Excavator) የታገዘ 5000 . የማህበረሰብ

አለታ ጩኮ ወረዳ ደበቃ ቀበሌ

1

84000

2

በቁፋሮ ማሸን (Excavator) የታገዘ 5000 . የማህበረሰብ

አለታ ጩኮ ወረዳ በዶንጎራ ሞሮቾ ቀበሌ

2

84000

3

የቦረቦር ልማት የጋቢዮን ግንባታ ስራዎች

አለታ ጩኮ ወረዳ በጉንዴ, ቀበሌ

3

30000

4

የቦረቦር ልማት የጋቢዮን ግንባታ ስራዎች

አለታ ጩኮ ወረዳ በዶንጎራ ሞሮቾ ቀበሌ

4

30000

 በዚሁ መሠረት ፡

  1. ደረጃቸው GC-9/BC-9 እና ከዚያ በላይ የሆነ የሥራ ተጫራጭ ማህበራት 2018 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታከለ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ።
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው መሥራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።
  3. በሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
  4. የስራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ሕጋዊ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  5. አንድ ተጫራች ተወዳዳሪ ከ አንድ ሎት በላይ መወዳደር አይችልም።
  6. የጨረታ ማስከበሪያ (bid security) ብር 84,000.00 (ሠማንያ አራት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና [BANK GAURANTE ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
  7. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፊቃዳቸውንና ተፅታ (VAT) የተመዘገበበትን ስርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ፋይናንስ ክፍል በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ላይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
  9. የጨረታው ስንድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security) ፣ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድረሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግዢ ከፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በወጣው በአስራ በአምስተኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታው ይከፈታል።ይሁንና ተጨራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  11. ከአሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይከወናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462124639 መደወል ይችላሉ

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ  ማስተባበሪያና አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-04-20
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በአስራ በአምስተኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-21 14:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: ሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የድጋፍ ማስተባበሪያና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 06, 2026
  • Posted at: 2026-04-07T10:45:27.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders