ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለኢትዮ ቴሌኮም ለሚያቀርባቸው ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውል ደንብ ልብስ (ጃኬት፣ ሱሪ እና ፖሎ ቲ-ሸርት)፣ ለድርጅታችን የስልጠና ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ ፕሮጀክተሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል

Description

INVITATION TO BID

CN/NCB/27/18

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር ለኢትዮ ቴሌኮም ለሚያቀርባቸው ሰራተኞች አገልግሎት ላይ የሚውል

  • ሎት1፡- ለኢትዮ ቴሌኮም ለሚያቀርባቸው ስራተኞች የሚውል ደንብ ልብስ (ጃኬት፣ ሱሪ እና ፖሎ ቲ-ሸርት)
  • ሎት 2፡- ለድርጅታችን የስልጠና ማዕከል አገልግሎት የሚውሉ ፕሮጀክተሮች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመግባት ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን ማስረጃ፣ የቲን ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በስም በታሽገ ሁለተኛ ኢንቨሎፕ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።

የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ አርብ (ጠዋት 2፡00-6፡00 እንዲሁም ከሠዓት 7፡00-11፡ 00) እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሠዓት ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1 ብር 100,000 እንዲሁም ለሎት 2 ብር 50,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።

ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ሚያዝያ 13 ቀን 2008 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ

ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር 011-156 9992

ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-21
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-04-21 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Commercial Nominees P.L.C.
  • Buyer TIN: 0000958158
  • Buyer address: ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Apr 08, 2026
  • Posted at: 2026-04-08T07:27:56.000Z
  • Buyer website: https://commercialnominees.com/

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders