የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ እና የስፌት አገልግሎት፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የውሃ ማጠራቀሚያ (ሮቶ) እና ፓምፕ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 02/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

  • ሎት 1. ደንብ ልብስ እና የስፌት አገልግሎት
  • ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት 3፡ የውሃ ማጠራቀሚያ (ሮቶ) እና ፓምፕ

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ

1. ተጫራቾች በተሠማሩበት የሥራ መስክ ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ እንዲሁም የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. አነስተኛና ጥቃቅን ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

3. የመንግሥት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው

4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 401 ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች ማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ የመጫረቻ የጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት CPO በማስያዝ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9. አቅራቢዎች ቫትን ከጠቅላላ ዋጋ ላይ አካተው ዋጋቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

10. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ስላሴ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት አምባሳደር ሞል ትምህርት ሚኒስቴር ጀርባ

ስልክ ቁጥር 011860325

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-04-20
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-20 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: አዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 08, 2026
  • Posted at: 2026-04-08T08:30:50.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders