በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ እና በሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የአገልግሎት ግዜያቸው ያበቁ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የሐራጅ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ እና በሴክተር መስሪያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የአገልግሎት ግዜያቸው ያበቁ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት፡-
- ሎት 1- ለኮንቲነሪ አገልግሎት የሚሆኑ ትላለቅ እና ወፍራም ብረቶች
- ሎት 2 የመኪና እና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎች
በዚህም መሰረት ማነኛውም ህጋዊ ድርጅት፣ ማህበር ወይም ግለሰብ በግልጽ ጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ፡-
- የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 /ሀያ ሺህ ብር ብቻ/ በጥሬ፣ በስፒኦ ወይም በባንክ ስሊፕ (ሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 1000268495812) ማስያዝ የሚችል ተጫራቾች ሰነዱን ከሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሪከርድ እና ማህደር ቢሮ በመምጣት የማይመለስ 200/ ብር ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በሚቶ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል መውሰድ የሚትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል ዶክመንት በሚገባ በመሙላት 01 /አንድ/ ኦርጅናል እና 02/ ሁለት ኮፒ ለየብቻ ቴክኒካል ዶክመንት 01 /አንድ/ ኦርጂናል እና 02 /ሁለት /ኮፒ ለየ ብቻ በተለያየ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ በማስገባት እና በማሸግ እና የሚመለከተውን የድርጅቱ ወይም የማህበሩ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል በመፈረም ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 06:00 ሰዓት ውስጥ ለጨረታው አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስገቢያ ቀን በተጠናቀቀበት ዕለት የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 06፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን 06፡30 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል። ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ከደረሰ ከመከፈት አይስተጓግልም።
ማሳሰቢያ፦
1.ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።
2. እቃዎች በያሉበት ቦታ ለማንሳት የማሽነሪ ወጪዎች በተጫራቹ የሚሸፈን ነው።
3. አሸናፊ ድርጅት ወይም ማህበር የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት ነው፡፡
4. የጨረታ ማስከበሪያ ከተጠየቀው መጠን አሳንሶ የሚያስገባ ተጫራች የጨረታ መስፈርት ያለሟሉ ተብሎ ውድቅ ይደረጋል።
5. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለ01 ወር ለሰላሳ ቀን ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 11 73 36 34/ 09 16 74 48 34/ 09 12 36 30 93 ይደውሉ
ሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
ሚቶ
Tender details
- Deadline: 2026-05-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ የስራ ቀናት 06:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-01 12:30
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 (ሀያ አንድ) ተከታታይ የስራ ቀናት 06:30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: ሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 08, 2026
- Posted at: 2026-04-08T09:12:43.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.