በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሶላር እና የፓምፕ እቃዎችን፣ ካሜራ፣ የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ግብርና ጽ/ቤት እና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት አገልግሎት የሚሆን በአስተዳደር ጽ/ቤት በጀት ከታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

  1. ሎት 1፡- ሶላር እና የፓምፕ እቃዎችን
  2. ሎት 2፡- ካሜራ
  3. ሎት 3 ፡- የደንብ ልብስ

በዚህም መሰረት ማንኛውም ህጋዊ ድርጅት ወይም ማህበር በግልጽ ጨረታው መሳተፍ የሚትፈልጉ፡-

  • በየመስኩ ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
  • ቲን- ነምበር ማቅረብ የሚችል
  • የቫት ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የአቅራቢዎች የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  • የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 20,000 /ሀያ ሺህ/ ብር ብቻ በጥሬ በሲፕኦ ወይም በባንክ ስሊፕ (ሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት 1000268495812) ማስያዝ የሚችል ተጫራቾች ሰነዱን ከሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሪከርድ እና ማህደር ቢሮ በመምጣት የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በሚቶ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል መውስድ የሚትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል ዶክመንት በሚገባ በመሙላት 01 አንድ/ ኦጅናል እና 02 / ሁለት ኮፒ ለየብቻ ፣ቴክኒካል ዶክመንት oı /አንድ/ ኦርጂናል እና ዐ2/ሁለት/ ኮፒ ለየ ብቻ በተለያየ ኢንቬፕ /ፖስታ/ በማስገባት እና በማሸግ የድርጅቱን ወይም የማህበሩን ማህተም በመምታት እና የሚመለከተውን የድርጅቱ ወይም የማህበሩ ባለቤት ወይም ህጋዊ ውክልና የተሰጠው አካል በመፈረም ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ዐ6፡00 ሰዓት ውስጥ ለጨረታው አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስገቢያ ቀን በተጠናቀቀበት ዕለት /በ15ኛው ቀን/ የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 06፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው ቀን 06፡30 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፤ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት ከደረሰ ከመከፈት አይስተጓግልም።

ማሳሰቢያ፡-

1. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

2. አሸናፊ ድርጅት ወይም ማህበር የሚለየው በእያንዳንዱ ሎት ነው።

3. የጨረታ ማስከበሪያ ከተጠየቀው አሳንሶ የሚያስገባ ተጫራች የጨረታ መስፈርት ያላሟላ ተብሎ ውድቅ ይደረጋል።

4. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ለዐ1 ወር/ሰላሳ ቀን/ ነው። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 11 73 36 34/ 09 16 74 48 34 /09 12 36 30 93 ይደውሉ

ሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

ሚቶ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /በ15ኛው ቀን/ የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 06፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-24 12:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /በ15ኛው ቀን/ የጨረታ ሳጥኑ ከቀኑ 06፡30 ሰዓት
  • Region: Central Ethiopia
  • Publishing entity: ሚቶ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Bid bond: 20,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Apr 08, 2026
  • Posted at: 2026-04-08T09:18:54.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders