የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የመጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር መመዝገቡን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፣ በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት መወዳደሪያ ኤንቨሎፑ ውስጥ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የጨረታው ዶከመንት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስና ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 05 ከ1፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል።
- ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሣሣይ ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች ብር 60,000.00 /ስልሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ዶክመንቱ ሲከፈት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው በሁለት ኮፒ መቅረብ አለባቸው።
- ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን እቃ የግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በእስፔስፊኬሽኑ እና በናሙናው መሠረት በ30 ቀናት ውስጥ በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በሚገኝበት መጋዘን አቅርቦ ማስረከብ አለበት።
- በዶከመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ወይም ሳምፕል ውጪ የሚቀርብ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈው ዋጋ 10% ውል ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በሁኔታ ያልተገደበ የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ መስጠት የሚችል መሆን አለበት።
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዢ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም።
- ባለሥልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03 ድሬዳዋ
ስልክ ቁጥር 025 112 4892
ፖ.ሣ.ቁ 44
ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-04-22
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-22 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Dire Dawa Administration Water Supply and Sewerage Authority
- Buyer address: ቀበሌ 03 ድሬዳዋ
- Bid bond: 60,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 08, 2026
- Posted at: 2026-04-08T09:23:43.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.