Spare parts and accessories

የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ላሉ ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ አቅርቦቶችን  በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ላሉ ተሸከርካሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

 ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ፈቃድ ያላቸው ።
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው።
  4. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  6. የሚገዙ እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከማ/አ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይቻላሉ።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 በመክፈል ማቅረብ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነና ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሐምሌ 27/2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 11/2018 ዓ.ም እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ን/አስ/ቡድን ክፍል ቢሮ ቁጥር 04 ነሐሴ11/2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 23 44 12 77 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  13. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

የማዕከላዊ አርማጭሆ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-08-17 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Central Armacheho Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Aug 03, 2026)
  • Posted at: 2026-08-04T08:56:39.000Z
← Back to all tenders