Spare parts and accessories
በአማራ ብ/ክ/መንግስት የደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት አገለግሎት የሚውሉ የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ለ1 ዓመት ውለታ፣ የመኪና ጎማ፣ የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት ለ1 ዓመት ውለታ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት ዕቃ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአማራ ብ/ክ/መንግስት የደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት አገለግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አቅርቦቶች መስፈርቱን ከሚያሟሉ ተጫራቾች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት- 1 የመኪና ዕቃ መለዋወጫ ለ1 ዓመት ውለታ
- ሎት-2 የመኪና ጎማ
- ሎት-3 የተሽከርካሪ ዘይትና ቅባት ለ1 ዓመት ውለታ
- ሎት-4 የጽህፈት መሳሪያ
- ሎት-5 የጽዳት ዕቃ
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ የሚችል፤
3. በተሰማሩበት የስራ መስክ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችሉ፤
4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ ሰፕላይ ሊስት/ ላይ የተመዘገበ፤
5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተጠቀሱትን ማሟላትና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 2019 ዓ/ም ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሚወዳደሩበት ሎት ጠቅላላ የሞሉትን ዋጋ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ሂ1 በማስቆረጥ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ማንኛው ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 2018 ዓ/ም 4፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኦርጂናል እና የማይመለስ ኮፒ የሥራ ፈቃድ እና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ይዘው በቀረቡበት ይህ ጨረታ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 2019 ዓ/ም 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡30 ሠዓት ደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል፡፡
10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 የተጠቀሰው ቢኖርም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታው ቀን ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፤
11. ጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ሆኖ ለመለየት አሻሚ ነገር መኖር የለበትም፡፡ ስርዝ ድልዝ ካለም ጨረታውን የሞላው አካል ስርዝ ድልዝ ስለመኖሩ መፈረም (ፓራፍ) ማድረግ ይኖርበታል፡፡
12. የጨረታ መክፈቻው ቀን በዕለቱ ከስራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
13. አሸናፊው አቅራቢ የሚለየው ለመኪና ዕቃ በየመኪኖቹ ሞዴል እና ጎማ በቀረቡት የጎማ አይነቶች ለየብቻ በጥቅል ዋጋ (Lot) ሲሆን ሌሎች ዕቃዎችንም በተመለከተ ለተጠየቁት ጠቅላላ ዕቃዎች በሙሉ በጥቅል ዋጋ (Lot) ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢው ይሆናል፡፡ በዚህ መስፈርት መሠረት ለሁሉም ዕቃዎች ዝርዝር ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0331118629 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብ/ክ/መንግስት የደሴ ከ/አስ/ገ/መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-08-24 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡30 ሠዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ደሴ ከ/አስ/ገ/አካ/ኢኮ/ል/መምሪያ
- Bid bond: 1.5%
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T07:59:26.000Z