የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የታሸጉ ውሃዎች ግዥ፣ የሕንፃ መሣሪያዎችና የፋብሪካ ውጤቶች ግዥ እና የሠራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የሚገዙ ዕቃዎች ዝርዝር (Lots):

  • ሎት-1፡ የተለያዩ የታሸጉ ውሃዎች ግዥ
  • ሎት-2፡ የሕንፃ መሣሪያዎችና የፋብሪካ ውጤቶች ግዥ
  • ሎት-3፡ የሠራተኞች የደንብ ልብስ ግዥ

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡- የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት።

  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚከተሉትን የጨረታ ማስከበሪያዎች በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO), በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው በተፈቀዱ የክፍያ ዘዴዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፦
  • ሎት-1፡ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
  • ሎት-2፡ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)
  • ሎት-3፡ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በሥራ ሰዓት ከጽሕፈት ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ዋጋቸውን በሰነዱ ላይ ያለ ስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላት፣ በሁሉም ገጾች ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍ፣ በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • በፖስታው ላይ የጨረታው ዓይነት፣ የተጫራቹ ስም እና ስልክ ቁጥር በግልጽ መጠቀስ አለበት:: ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ሳጥኑ በ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ፣ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽሕፈት ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ክፍል ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል።
  • አሸናፊው አካል የዕቃውን ጥራትና ወቅታዊነት ጠብቆ እስከ መሥሪያ ቤቱ ድረስ የትራንስፖርትና የአውራጅ ወጪ ችሎ የማስረከብ ኃላፊነት ይኖርበታል።
  • የዕቃ ጥራት ጉድለት በሚታይበት ጊዜ አቅራቢው ወዲያውኑ የመቀየርና የማስተካከል ግዴታ አለበት።
  • ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
  • በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማና ማህተም መደረጉን ደግመው ያረጋግጡ
  • አድራሻ፡- የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት

ስልክ፡- 09 83 26 16 48

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-27
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-27 14:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከሰዓት 8፡00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Arba Minch Zuria Finance and Economic Development Chief Bureau
  • Buyer address: አርባ ምንጭ ከተማ ከዋናው ማዘጋጃ ከፍ ብሎ በአዲሱ ህንፃ ላይ እንገኛለን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 09, 2026
  • Posted at: 2026-04-09T08:30:43.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders