በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ በጋሞ ዞን የአምንጭ ዙ/ወረዳ የፋይናንስና ፕላን ልማት ጽህፈት ቤት፤ በመስሪያ ቤቱ የሚገኙ የተለያዩ ደረጃ ያላቸውን ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች፣ ያገለገሉ ባለሁለት እግር ያማሃ ሞተር ሳይክሎች እና ያገለገለ ቶዮታ ፒካፕ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ በጋሞ ዞን የአምንጭ ዙ/ወረዳ የፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት፤ በመ/ቤቱ የሚገኙ የተለያዩ ደረጃ ያላቸውን ያገለገሉ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም የቤት ክዳን ቆርቆሮዎች ፤ ያገለገሉ ባለሁለት እግር ያማሃ ሞቴር ሳይክሎች እና ያገለገለ ቶዮታ ፕካፒ መኪና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፦
ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በመሥሪያ ቤታችን የግዥ ኬዝ ቲም ክፍል ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት ፐርሰንት) የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ሁሉም ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ከመሙላታቸው በፊት ዕቃው የሚገኝበትን ደረጃ በመሥሪያ ቤታችን ግቢ ውስጥ ተገኝተው ማየት ይኖርባቸዋል፡፡ ዕቃውን ሳያዩ ዋጋ ሞልተው በኋላ ላይ የሚመጣ ማንኛውም ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም።
ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ፣ በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል፡፡ (16ኛው ቀን በዓል ወይም የሳምንት ዕረፍት ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከናወናል)።
የጨረታው አሸናፊ ውጤቱ ከተገለጸለት በኋላ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ገንዘብ በጽሕፈት ቤቱ የባንክ ሂሳብ ገቢ በማድረግ በ 5 የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቃውን ማንሳት ይኖርበታል።
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈጽሞ ዕቃውን የማያነሳ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል።
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፦ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ ቁጥር፡ 09-83-26-16-48
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት፣ በጋሞ ዞን
የአ/ምንጭ ዙ/ወረዳ የፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-27
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከረፋዱ 5:00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-27 14:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 8:00 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Arba Minch Zuria Wereda Finance and Economic Deveoplment Chief Auditor’s Bureau
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 09, 2026
- Posted at: 2026-04-09T08:34:13.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.