የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ደንብ ልብስ እና የስፌት አገልግሎት፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የውሃ ማጠራቀሚያ (ሮቶ) እና ፓምፕ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Description
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት 1. ደንብ ልብስ እና የስፌት አገልግሎት
- ሎት 2. የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 3. የውሃ ማጠራቀሚያ (ሮቶ) እና ፓምፕ
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ
1. ተጫራቾች በተሠማሩበት የሥራ መስክ ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ እንዲሁም የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. አነስተኛና ጥቃቅን ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
3. የመንግሥት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ፈቃድ ያላቸው
4. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 401 ማግኘት ይችላሉ።
6. ተጫራቾች ማስታወቂያ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ የመጫረቻ የጠቅላላ ዋጋ 2 ፐርሰንት CPO በማስያዝ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሽያል ኦርጅናልና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ሞልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. አሸናፊ ተጫራች የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 ፐርሰንት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. አቅራቢዎች ቫትን ከጠቅላላ ዋጋ ላይ አካተው ዋጋቸውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ሥላሴ ቤተክርስቲያ ፊት ለፊት አንባሳደር ሞል ትምህርት ሚኒስቴር ጀርባ
ስልክ ቁጥር 0118603257
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-04-21
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-04-21 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛዉ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አዲስ አበባ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 09, 2026
- Posted at: 2026-04-09T09:23:01.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.