የዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ለሴፍቲኔት ፕሮግራም ግልጋሎት የሚውል የኢንዳስትርያል ማቴሪያል /industrial material /፣ ሎካል ማቴሪያል /Local material/፣ ብሎኬት በአለም ባንክ ለፕሮጀክት ማስፈፀምያ ተብሎ ከፀደቀ በጀት በሃገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ለሴፍቲኔት ፕሮግራም ግልጋሎት የሚውል

  • በሎት-1 የኢንዳስትርያል ማቴሪያል /industrial material /፣
  • በሎት 2 ሎካል ማቴሪያል /Local material/
  • በሎት-3 ብሎኬት በኣለም ባንክ ለፕሮጀክት ማስፈፀምያ ተብሎ ከፀደቀ በጀት በሃገራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ስለሚፈልግ

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ለምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  • ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ መለያ ቁጥር /Tin No/፣ የዘመኑ የታደሰ የመቅረባይነት ሰርተፊኬት/በኦን ላየን በፌዴራል በአቅረባይነት ዝርዝር የተመዘገበበት ማስረጃ፣ የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬትና ጊዜው ያላላፈው የቫት ዲክላሬሽን ቅጂ ከዋናው ዶክመንት ማቅረብ የሚችል።
  • ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ይህ ምልክታ ጨረታ ከወጣበት ቀን 1 ሚያዝያ 2018 ዓ.ም እስከ ቀን 30 ሚያዝያ 2018 ዓ/ም 11:30 ሰዓት የማይመለስ ብር 400.00 /ኣራት መቶ እየከፈላችሁ ከዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት በግዥ ቢሮ ቁጥር 7 ሰነድ መውሰድ ትችላላችሁ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ ሰዓት በፊት ለሎት- 1 ለኢንዳስትርያል ማቴሪያል/industrial material/ በኢትዮዽያ ገንዘብ 50000.00 /ኣምሳ ሺ ብር/፣ ለሎት 2 ለሎካል ማተርያል/ Local material/ በኢትዮዽያ ገንዘብ 40000.00 /ኣርባ ሺ ብር/፣ ለሎት3 ለብሎኬት 20000 /ሃያ ሺ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ክረዲት ሌተር፣ በሲፒኦ ወይ በጥሬ ገንዘብ የጨረታ ማስከበርያ ማስያዝ ኣለባቸው።
  • የጨረታ ሳጥን በከተማ ዓዲግራት ዕቅድና ፋይናንስ የሚገኝ ሲሆን ይህ ምልክታ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተጫራቾች ክፍት ይሆናል።
  • ጨረታው ግንበት 3/2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰአት ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት ተጫራቾች ወይ ደሞ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • የሚሞላው ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ የባለቤቱ ፊርማ መደረግ አለበት
  • የጨረታ ኣሸናፊ የሚሆነው በየሎቱ በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ የሞላ ተጫራች ይሆናል
  • የሚሞላው ዋጋ ከነቫቱ መሆኑና ኣለመሆኑ ሊገለፅ ይገባል፤ካልተገለፀ ደሞ የተሞላው ዋጋ ግዥ ፈፃሚ ኣካል ከነቫቱ መሆኑን ታሳቢ ያደርጋል።
  • በእያንዳንዱ የመጫረቻ ሰነድ ማህተምና ፊርማ የባለቤቱ መደረግ ይገባቸዋል።
  • መስሪያ ቤታችን ይህ ጨረታ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ ማብራሪያ በስራ ሰዓት በኣካል ወደ ቢሯችን በመምጣት ወይም ደሞ በሞባይል ቁጥር፡- 0914123546 ወይም 0941336816 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-11
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-05-11 10:30
  • Region: Tigray
  • Publishing entity: ዓዲግራት ከተማ ዕቅድና ፋይናንስ ፅህፈት ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 400.00 /አራት መቶ ብር/
  • Published: Apr 09, 2026
  • Posted at: 2026-04-09T09:34:44.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders