የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከበውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘረውን ንብረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረቶቹ ዓይነት ዝርዝር |
ታርጋ ቁጥር |
የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) |
ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ |
የጨረታ ሁኔታ |
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ኤም ቱኬ ኢንጅነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ |
ማሽነሪዎች እና እኩፕመንት |
|
ብር 34,781,495.00 (ሰላሳ አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ አራት መቶ ዘጠና አምስት ብር) |
ገላን ከተማ ኤም ቱኬ ኢንጅነሪንግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
ድርድር |
ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት |
|
2 |
የቢሮ ዕቃዎች |
|
ብር 650,051.00 (ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ ሃምሳ አንድ ብር) |
ገላን ከተማ ኤም ቱኬ ኢንጅነሪንግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
ድርድር |
ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት |
|
|
3 |
ፎርክሊፍት |
|
ብር 210,396 (ሁለት መቶ አስር ሺህ ሦስት መቶ ዘጠና ስድስት ብር) |
||||
|
4 |
ጀነሬተር |
|
ብር 697,151 (ስድስት መቶ ዘጠና ሰባት ሺህ አንድ መቶ ሃምሳ አንድ ብር) |
||||
|
5 |
ቶዮታ ሚንባስ |
3-77195 አአ |
ብር 763,853.00 (ሰባት መቶ ስልሳ ሦስት ሺህ ስምንት መቶ ሃምሳ ሦስት ብር) |
ለገጣፎ ለገዳዲ በቀድሞ ኤም ኤን ኤስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
|||
|
6 |
ቶዮታ ሚንባስ |
3-65018 አአ |
ብር 2,202,545.00 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሁለት ሺህ አምስት መቶ አርባ አምስት ብር) |
||||
|
7 |
ካርጎ ትራክ |
3-01-77197 አአ |
ብር 410,562.00 (አራት መቶ አስር ሺህ አምስት መቶ ስልሳ ሁለት ብር) |
ገላን ከተማ ኤም ቱኬ ኢንጅነሪንግ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ |
|||
|
8 |
ካርጎ ትራክ |
3-77150 አአ |
ብር 342,940.00 (ሦስትመቶ አርባ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ አርባ ብር) |
||||
|
9 |
ካርጎ ትራክ |
3-77196 አአ |
ብር 345,355.00 (ሦስት መቶ አርባ አምስት ሺህ ሦስት መቶ ሃምሳ አምስት ብር) |
ማሳሰቢያ፤
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ለማሽነሪዎች (ተ.ቁ 1) እና ግንቦት 04 ቀን 2018 ዓ.ም ሌሎች ንብረቶች (ከተ.ቁ 2-9) ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ግንቦት 03 እና 04 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
2. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መከፈል ይኖርበታል፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወክሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ (ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
6. አንዳንድ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ/ታክስ ለመንግስት ለመክፈል ይገደዳል።
7. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል።
8. የንብረቱ ስመ-ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል:: ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።
9. የጨረታ አሸናፊው ማሽነሪዎችን ለመንቀልና ለማጓጓዝ የሚያስፈልግ ወጪ በራሱ ይሸፍናል።
10. ንብረቶቹ ለጨረታ የቀረቡት በየተራ ቁጥሩ በተናጠል ነው።
11. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንሰርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ ኣሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73 / 011-524-42-69 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
12. ተጫራቾች አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹን መጎብኘት ይችላሉ።
13. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
Tender details
- Deadline: 2026-05-12
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-05-12 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Apr 09, 2026
- Posted at: 2026-04-09T09:43:35.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.