የመኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ /ባለመበት አቶ አሸናፊ ዘነበ እና የፍ ባለዕዳ አቶ አለማየሁ ግርማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቁጥር 208456 በ14/02/2018 ዓ/ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ 212080 በህዳር 18 ቀን 2018 ዓ/ም ጥር 25 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠቁ ኮድ 2-C07896 አ/አ vitz የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 950,000 (ዘnኝ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ምንም ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.212080 በቀን መጋቢት 16 ቀን 2018ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 237,500 (ሁለት መቶ ሰላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ) ሆኖ የስም ማዛወሪያ ግዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 22 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 9፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሸያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተርተው ለሙግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሎት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመበቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፈፍ ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመበቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ዝዓዘብ ገቢ ሳይደረማ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-30
- Bid closing time: 15:00
- Bid opening: 2026-04-30 15:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 10, 2026
- Posted at: 2026-04-11T07:18:06.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.