በየካ ክፍለ ከተማ ጤ/ጽ/ቤት ጉራራ ጤና ጣቢያ አላቂ የሕክምና ዕቃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

3ኛ ዙር አጠቃላይ ገዥ የጨረታ ማስታወቂያ

በየካ ክ/ከተማ ጤ/ጽ/ቤት ጉራራ ጣቢያ

  • ሎት 1፡- አላቂ የሕክምና ዕቃዎች

ስለሆነም በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች

1. ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣

3. ግብር የመክፈል ግዴታ የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር አስገቢው ባለሥልጣን ማስረጃ የሚያቀርብ ፣

4. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጉራራ ጤ/ጣቢያ ግዥ ክፍል ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ከ 5/8/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ-ሐሙስ ጠዋት ከ2፡30-6፡00 እና ዓርብ ከ2፡30-5፡00 እና ከሰዓት ከሰኞ-ዓርብ ከ7፡30-11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፤

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000.00 ብር (አስር ሺ ብር) ሲፒኦ በማሠራት ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል (ከሲፒኦ ውጭ የሆኑ ዋስትናዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም)፤

6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ፖስታ ለይቶ በማሸግ የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ5/8/2018 ዓ.ም ጀምሮ አስራ አንደኛው የሥራ ቀን 4፡00 ድረስ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ብረት ድልድይ የሃ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ጉራራ ጤ/ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ግዥ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤

7. ተጫራቾች በሙሉ ወይም በከፊል መወዳደር ይችላሉ፤

8. ተጫራቾች ከውድድር በኋላ አሽናፊ ከሆኑ ላሸነፉት እቃ የጠቅላላ ዋጋውን 10% የውልማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን በ19/08/2018 ዓም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሣጥኑ ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በጽ/ቤቱ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

10. መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0910275044/ 0913062744/ መደወል ይቻላል።

አድራሻ፡- ፈረንሳይ ለጋሲዮን ብረት ድልድይ የሃ ት/ለፊት

በየካ/ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ጉራራ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-27
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-04-27 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gurara Health Post
  • Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published: Apr 11, 2026
  • Posted at: 2026-04-11T07:52:56.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders