የንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

Description

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ምዕራብ የገበያ አዳራሽ አ.ማ እና በፍ ባለዕዳ ወ/ሮ አስቴር ጥበቡ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 71434 በ02/02/2013ዓ.ም እና መቁ 81624 በ4/8 /2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የፍ/ባለመብት ግቢ ውስጥ የሚገኙ ንብረቶች የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 193,490 (አንድ መቶ ዘጠና ሶስት ሺህ አራት መቶ ዘጠና ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 30 ቀን 2018 ዓም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ9፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፈደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፤ ንብረቱን ተጣርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPOማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ  የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አጽ/ ቤት/ስም CPO አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደረጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዞወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-08
  • Bid closing time: 15:30
  • Bid opening: 2026-05-08 15:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
  • Bid bond: 25%
  • Published: Apr 11, 2026
  • Posted at: 2026-04-11T08:42:44.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders