የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአስኮ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 02/2018ዓ. ም
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአስኮ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዝሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፊቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ(ቲን ነምበር)ቁጥር ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ(የቫት)ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስከር ወረቀት ያላቸው
- ያቅራቢነት ሊስት ስለመመዝገባቹ በዌብ ሳይት ይረጋገጣል
- ናሙና(ሳምፕል) ለሚጠይቁ እቃዎች ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 0.5 % በየሎቱ ለሎት 1፡- 35,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ 1. (ሲፒኦ) ፤ 2. የዋጋ መሙያ ሰነድ ፤ 3. የሰነዱ ኮፒ እያንዳዳቸው ለብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ሶስት ፖስታ አምጥተው ቢሮ ቁጥር 56 ለዚህ በተዘጋጅው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ 7ኛው ቀን ጅምሮ ውል ተዋውለው የውል ማስረከቢያ ባሸነፈባቸው እቃዎች ላይ 10 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማሲያዝና እቃዎቹን ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ሰነዶች በአንድ ሰነድ ውስጥ ያሉ በመሆናቸው መወዳደር እና ዋጋ ሞልታቹ ማስገባት የምትችሉት ባላቹ የንግድ ፍቃድ ዘርፍ መሆኑን አውቃቹ በከፍል አራት የእንድ ዋጋ እና በክፍል ስድስት ያለውን አስፐስፍኬሽን በጥንቃቄ አይታቹ እንድትሞሉ እና የዋጋ ማቅረቢያ ላይ የሚሞላው ቫትን ጨምሮ መሆኑን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፐ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት ቢሮ ቁጥር 56 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር የስራ ሰዓት ከ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ አስኮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 56 በመኘት የማይመለስ 300 ብር (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ለጥቃቅን እና አነሰተኛ ለአምራች ዘርፍ ብቻ የሚሰጥ ሲሆን ለዚውም የዋስትና ደብዳቤ ከአደራጃቸው አካል ሲያቀርቡ ነው
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ10 የስራ ተከታታይ ቀናት ማስገባት የሚቻል ሲሆን በመጨረሻው ቀን 11፡30 ላይ ማስገባት የሚያበቃ ሲሆን በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ላይ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን ዕቃ በሚያቀርብበት ሰዓት በራሱ ትራንስፖርት ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ያስረከባል፡፡
አድራሻ ፡- ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ብርጭቆ ፋብሪካ ፊት ለፊት ሚኪሊላንድ ኮንዶሚኒየም መግቢያ ላይ
አስኮ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ነው፡፡ ስልከ ቁጥር፡- 0911908647 / 0961013560
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአስኮ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-24
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ10 የስራ ተከታታይ ቀናት ማስገባት የሚቻል ሲሆን በመጨረሻው ቀን 11፡30 ላይ ማስገባት የሚያበቃ ሲሆን በ11ኛ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-24 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለ10 የስራ ተከታታይ ቀናት ማስገባት የሚቻል ሲሆን በመጨረሻው ቀን 11፡30 ላይ ማስገባት የሚያበቃ ሲሆን በ11ኛ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Asko Secondary School
- Bid bond: 35,000 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 12, 2026
- Posted at: 2026-04-13T08:34:58.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.