በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ያገለገሉ መኪና መለዋወጫ፣ የመኪና ቦዲና ቀርጥራጭ ብረቶች በሎት ጠቅላላ ድምር ዋጋ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ያገለገሉ መኪና መለዋውጫ የመኪና ቦዲና ቀርጥራጭ ብረቶች በሎት ጠቅላላ ድምር ዋጋ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስስዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾቾ መወዳደር ይችላሉ።
1. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የመኪና መለዋጫዎች የመኪና ቦዲና ቁርጥራጭ ብረቶች በአንድ ጊዜ በራሱ ትራንስፖርት ከንብረት ክፍል ማንሳት የሚችል መጫረት ይችላል።
2. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህትም ማድረግ ኣለባቸው።
3. የሚጫቱበትን የአንድ ኪሎ ግራም ብረት ዋጋ በመጥቀስና በታሸገ ፖስታ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣ ቀን ጀምሮ 15 ተከታይ ቀናት በደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ድሮው ንግድ ባንክ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይቻላል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር በመክፍል የደ/ማከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ድሮው ንግድ ባንክ ማግኘት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች በሚሞሉት ዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም።
6 ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ C.P.O ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በደ/ማ ከኤስ ገንዘብ መምሪያ ስም በተዘጋጀ መሂ 1 ደረሰኝ 20000 /ሃያ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባችዋል፡፡
7. የአንድ ኪሎ ግራም ብረት የጨረታ መነሻ ዋጋ 69 /ስልሳ ዘጠኝ ብር/ ነው።
8. ማንኛውም ተጫራች ሰነዱን ሞልቶ በታሸገ ፖስታ ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት የቀድሞው ዋናው ንግድ ባንክ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት የሚቻል ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ በአየር ላይ ይውላል።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የደ/ማ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቅጥር ግቢ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል የጨረታ መክፈቻው የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራተን የሚከፈት ይሆናል።
10. አሸናፊው ግለሰብ/ድርጅት/ የአሸነፋቸውን ብረታ ብረት የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በመክፈል በ10 ቀናት ውስጥ ማንሳት አለበት።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587713362
በአብክመ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-04-27
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሠዓት
- Bid opening: 2026-04-27 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሠዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
- Published: Apr 12, 2026
- Posted at: 2026-04-13T10:00:57.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.