የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
1. የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ጨረታ ቁጥር 008/2025/26
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብዛታቸው 3 የሆኑ የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በድጋሚ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሚያዝያ 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራች ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ከሚያዝያ 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አለፍ ብሎ በሚገኘው በባንኩ የተሽከርካሪ ጋራዥ /የቀድሞ አማልጋ ሜትድ/ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
3. የተዘጋጅው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።
4. ተጫራቾች ለተሽከርካሪው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሠነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባሉ።
5. ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ ፎቅ በግልጽ ይከፈታል።
6. የተሽከርካሪዎቹ ዓይነትና ታርጋቸው የሚያሳይ ዝርዝር
|
S.No. |
Types of Vehicles |
Vehicles Plate Number |
|
1 |
Bishoftu double cabin Pickup |
3-98853 ET |
|
2 |
Bishoftu double cabin Pickup |
3-53224 ET |
|
3 |
Bishoftu double cabin Pickup |
3-98890 ET |
2. በድጋሚ የወጣ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ጨረታ ቁጥር 009/2025/26
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተለያዩ ንብረቶችን ማለትም የተለያዩ ያገለገሉ ጀነሬተሮች የተለያዩ ያገለገሉ የተሸከርካሪ ጎማዎች፣ የተለያዩ ያገለገሉ የተሸከርካሪ ባትሪዎች፣ የቪ8 ተሸከርካሪ ዕቃ መጫኛና የአልሙኒየም ጀርካኖች ፣የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ የተቃጠለ የሞተር ዘይት፣ የተለያዩ ያገለገሉ ካርቶኖች፣ ንቃይ ቴለር ካውንተሮችና የእንጨት ፓሌቶች እና የተለያዩ ከተሽከርካሪ የተፈቱ ብረታ ብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. ስለ አሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሚያዝያ 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
2. ተጫራች ያገለገሉ ንብረቶችን ከሚያዝያ 06 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያገለገሉ ንብረቶችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ እና የተቃጠለ የሞተር ዘይት የሚገኘው ቃሊቲ ከመንገድ ትራንስፖርት የማሽከርከር ብቃት ማረጋገጫ እና ማሰልጠኛ ተቋም አጠገብ በሚገኘው የባንኩ ተሽከርካሪዎች ጥገና ጋራዥ /የቀድሞው አማልጋ ሜትድ/ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል።
3. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል።
4. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል።
5. የተቃጠለ የሞተር ዘይትና ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን የማስወገድ ወይም መልሶ ለመጠቀም ከኢፌድሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ፈቃድ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
6. ሚያዚያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 2ኛ ፎቅ በግልጽ ይከፈታል።
ተጫራች ለሚጫረትበት የንብረት ዓይነቶች የጨረታ የመነሻ ዋጋውን 25% (ሃያ አምስት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለያገለገሉ ንብረቶች አስወጋጅ (Commercial Bank of Ethiopia Disposal) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
Tender details
- Deadline: 2026-05-06
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-05-06 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Commercial Bank of Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Apr 12, 2026
- Posted at: 2026-04-14T11:42:13.000Z
- Buyer website: https://www.combanketh.com
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.