የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የእንስሳት መኖ መግዛት ይፈልጋል
Description
ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
NCB 003/2018
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የቀረበውን ግዥ በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ NCB 003/2018 አወዳድሮ የእንስሳት መኖ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ በመንግሥት ግዥ ላይ ለመሳተፍ የተመዘገቡበት የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የግብር ከፋይነት ቲን ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተቀመጠው ቀንና ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ቢድ ቦንድ ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ የተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ስም ሞልተው ከኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦሪጅናልና በአንድ ኢንቨሎፕ ታሽጎ ኮፒ ተደርጎ መቅረብ አለበት:: የኮፒ ሠነዶች ከኦሪጅናል ሠነዱ ጋር በአይነትም ሆነ በብዛት ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡የጨረታውን ስምና ቁጥር በመግለጽ በኮርፖሬሽኑ ግዥ ዲፓርትመንት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ተዘግቶ ከረፋዱ 5፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ሸጎሌ ጊቢ ግዥ ዲፓርትመንት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የመንግሥት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ ይከፈታል።
6. ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር /011-517-25-21/11 ደውለው ወይም በአካል መጠየቅ ይችላሉ።
7. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-04-28
- Bid closing time: 11:30
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-28 11:45
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡45 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Broadcasting Corporation
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Apr 13, 2026
- Posted at: 2026-04-14T11:57:34.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.