Pharmaceuticals and medicines

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ የተለያዩ መደሀኒቶችና ሪኤጀንቶች ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

(የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ፈ/ህ/ጤ/ጣ/ 002/2018)

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ለ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ የተለያዩ መደሀኒቶችና ሪኤጀንቶች፣ ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ ተወዳዳሪዎችም ማቅረብ ያለባቸው መረጃዎች

  • በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው
  • በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላችሁ
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  • በአቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ውስጥ የተመዘበበትን መስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  • የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት
  • የጨረታ ሰነዱን 200.00 ሁለት መቶ ብር/ በመግዛትና የጨረታ ሰነዱን በትክክል በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸሁ
  • የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትናን በሚመለከት ተጫረቾች በሚወዳደሩበት አቀርቦት ላይ (CPO)ማሲያዝ ይኖርባቸዋል።

ተ.ቁ

የእቃው አይነት በሎት

ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ወይም ቅድመ ሁኔታ ባስቀመጠው የባንክ ዋስትና

ሎት 1

የተለያዩ መድሀኒቶችና ሪኤጀንቶች

5000.00

  • ለተሸነፊዎች የጨረታ ማስከበሪያ በ15 ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል።
  • አሸናፊ ከሆኑ የውል ማስረከቢያ ባሸነፈው ዋጋ ልክ 10% ያሲዛሉ
  • ጤና ጣቢያው ጨረታውን የተሻለ መንገድ ካገኘ በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ጨረታውን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአትና ቀን ማስገባት አለባቸው
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ4፡ዐዐ ሰዓት የሚከፈት ሲሆን አስራ እንደኛው ቀን ግን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው በተዘጋጀው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
  • ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ ላይ በተገለጸው መሰረት ምንም አይነት ማሻሻያ ሳያደረጉ መሙላት አለባቸው ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።

ማሳሰቢያ፦ የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ኦርጅናሉንና ኮፒውን በሁለት ፖስታ አሽጋችሁ ማስገባት አለባችሁ።

ከላይ የተጠቀሰውን ማስረጃዎቻችሁን በኮፒው የጨረታ ሰነድ ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ

አድራሻ፡- ወረዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም አጠገብ ከሀሌሉያ ሆስፒታል ጎን

ስልክ ቁጥር- 011 866 81824/20

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ ቤት

የፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-04-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-24 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Felege Hiwot Health Post
  • Buyer address: በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 04 ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ጎተራ ኮንደሚኒየም ሙሉ ወንጌል ቸርች አጠገብ
  • Bid bond: 5000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Apr 13, 2026)
  • Posted at: 2026-04-14T12:16:40.000Z
← Back to all tenders