በሕግ በመፍረስ ላይ ያለው የብሔራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት ያገለገሉ የቆርቆሮ መጋዘኖችን በራሱ ወጪ በማፍረስ ቆርቆሮዎችን እና ፍራሽ እንጨቶችን እንዲሁም የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጥቅል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የቆርቆሮ መጋዘኖችን እና ሌሎች የቢሮ ዕቃዎችን

ለመሸጥ በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 01/2018

በሕግ በመፍረስ ላይ ያለው የብሔራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት ያገለገሉ የቆርቆሮ መጋዘኖችን በራሱ ወጪ በማፍረስ ቆርቆሮዎችን እና ፍራሽ እንጨቶችን እንዲሁም የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጥቅል በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል ።

ስለሆነም፡-

1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ስዓት የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ /በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል፡፡

2. የጨረታ ሰነዱን ከገዙበት ቀን ጀምሮ ኮተቤ በሚገኘው ብሔራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት ግቢ በመገኘት ንብረቶቹን መመልከት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቹ ለመጫረት ከሚያቀርበው ዋጋ 10% የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ /Bid Bond/ በባንክ በተመሠከረለት ቼክ /CPO/ በመ/ቤቱ ትክክለኛ ስም በማሠራት ከጨረታ ሠነዱ ጋር በማያያዝና በፖስታው ላይ የተጫራቹን ስምና አድራሻ በመግለጽ እስከ ጨረታው መዝጊያ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 2- ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡

4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤቱ መሠብሠቢያ አዳራሽ ሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል።

5. በቂ የዋስትና ማሰከበሪያ CPO ያላስያዙ ተጫራቾች ኮሚቴው ከጨረታው የመሰረዝ መብት አለው፡፡

6. የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሽናፊዎች የጨረታ ውጤት እንደፀደቀ ይመለስላቸዋል፡፡

7. ተጫራች ያሸነፋቸውን መጋዘኖች በራሱ ወጪ በማፍረስ እና በትራንስፖርት በተሰጠው ጊዜ ገደብ ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል፡፡

8. የጨረታው አሸናፊዎች በውጤቱ መሠረት ከፍያውን ከፈፀሙ በኋላ ያሽነፋባቸውን ንብረቶች በ15 ቀናት ውስጥ መጋዘኖችን በማፍረስ ቆርቆሮዎቹ እና ፍራሽ እንጨቶችን አንስተው ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡

9. ከላይ በተጠቀሰው 15 ቀናት ውስጥ ንብረቱን አጠናቆ ያልወሰደ ተጫራች የጥበቃና የቦታኪራይ በቀን ብር 500.00 እንዲከፍል ይደረጋል፡፡

10. መ/ቤቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ከአራራት ሆቴል ወደ ወሰን በሚወሰደው አዲስ አስፋልት ከፍ ብሎ አቤም ሆቴል ፊት ለፊት፡፡

ስልክ ቁጥር 0913 019 601

በሕግ በመፍረስ ላይ ያለ የብሔራዊ መሐንዲሶችና ሥራ ተቋራጮች ድርጅት

አዲስ አበባ


Tender details

  • Deadline: 2026-05-07
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-05-07 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: National Engineers Contractors Enterprise
  • Buyer address: ከአራራት ሆቴል ወደ ወሰን እና ካራ በሚወስደው አዲሱ አስፋልት ከሰንሻይን ሪል እስቴት ከፍ ብሎ ካለው መስቀለኛ መንገድ ሲደርሱ ፊት ለፊት ነው
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 14, 2026
  • Posted at: 2026-04-14T12:47:39.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders