በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2018 በጀት አመት ዲጅታል ቪዲዮ ካሜራ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን በ2018 በጀት አመት በግልጽ ጨረታ በድጋሜ የወጣ 1, ዲጅታል ቪዲዮ ካሜራ 2, ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
4. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ከ ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች በግልፅ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. የግዥው መጠን ከ 20,000 (ሀያ ሺ ብር) በላይ ከሆነ 15 በመቶ ተጨማሪ እሴት ታክስ ላይ 50 በመቶ የሚቆረጥባቸው መሆኑን ማወቅ አለባቸው
7. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፣
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 (ሀምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ከግዥ ፋይ/ንብ/አስዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 17 ማግኘት ይቻላል፣
9. የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል፡፡
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
11. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ አንድ ፖስታ በግዥ ኦፊሰር ቢሮ ቁጥር 14 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 15ኛዉ ቀን 11፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 14- በ16ኛዉ ቀን በ30፡00 ሰዓት ታሽጐ 3፡30 ሠዓት ይከፈታል፣
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 0583205838 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 0583207104 ወይም 0582266035 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፣
አድራሻ ባህር ዳር ቀበሌ 13 ከስፖርት ኮሚሽን ጀርባ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን
Tender details
- Deadline: 2026-04-28
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን በ3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-04-28 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ ቀን በ3፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: ANRS Prison Administration Commission
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 50.00 ብር
- Published: Apr 13, 2026
- Posted at: 2026-04-15T08:04:11.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.