ሪሪ ፕሮጀክት ዴቨሎፐር ኃላ/የተ/የግ/ማህበር 22,500 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ያገለገሉ/ውድቅዳቂ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ያገለገሉ ብረታ ብረቶች ሽያጭ ግልጽ ጨረታ
ድርጅታችን 22,500 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ያገለገሉ/ውድቅዳቂ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም
1. ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ያገለገሉ ብረት ብረቶች ጫንጮ በሚገኘው የድርጅታችን ፋብሪካ በመቅረብ (በስራ ቀን እና በስራ ሰዓት) መመልከት ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃዳቸውን በማያያዝ ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 6፡00፤ ከሰዓት ከ7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 በታሸገ ፖስታ አድርገው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ላምበረት ላሜዴይሪ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቢሯችን እስከ ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
3. ጨረታው የሚከፈተው ሚያዝያ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ላምበረት ላሜዴይሪ ህንፃ በሚገኘው በዋናው መ/ቤት ስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነው።
4. አሸናፊ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ሙሉ በሙሉ በመክፈል ያገለገሉ ብረታ ብረቶችን በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ይኖርባቸዋል።
5. አሸናፊዎች ባሸነፉበት ዋጋ ላይ ለመንግስት የሚከፈል 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተ.እ.ታ ይከፍላሉ።
6. ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠነቀ ነው።
7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0986 061 366 ወይም 0913 301 160 ይጠቀሙ።
ሪሪ ፕሮጀክት ዴቨሎፐር ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-04-17
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-04-17 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ሪሪ ፕሮጀክት ዴቨሎፐር ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
- Published: Apr 15, 2026
- Posted at: 2026-04-15T11:26:58.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.