የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት የሶስት ወር ዶሮ እና የሶስት ወር ዶሮ መኖ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ማስታወቂያ

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ል/ት/መምሪያ የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት ለደባይ ጥላት ግን እንስሳት እና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት በሰቆጣ ቃል ኪዳን በጀት

  • ሎት 1. የሶስት ወር ዶሮ እና 
  • ሎት 2. የሶስት ወር ዶሮ መኖ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሞሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።

  1. ከላይ በተጠቀሱት ስራ ዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎችን ማያያዘ እንዲሁም የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  2.  ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱት እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሎት 1. ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር) ሎት2. ብር 5,000 (አምስት ሽህ ብር) ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  4. የጨረታ አሸናፊ የሚሆነው ዝቅተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች በጨረታው አሸናፊ ይሆናል።
  5. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን 11:30 ድረስ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በስም በታሸገ ፓስታ በደ/ጥ/ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን ክፍል ለዚሁ ለተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው በ16ኛ ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ጀምሮ የሚከፈት ይሆናል፡፡ አሸናፊ ተጫራች ያሸነፈባቸውን ጠቅላላ እቃዎች ከደባይ ጥላት/ግን/ወ/ ግብርና ፑል ንብረት ክፍሎች ድረስ በመምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
  8. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በዓል ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል።
  9. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  10. የዶሮዎችን የእድሜ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  11.  የዶሮዎችን የክትባት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  12.  ዶሮዎች ወደ ፋርሙ የገቡትን ቀን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቁጥር 058 257 02 57 /01 43 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የደባይ ጥላት ግን ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-04-28
  • Bid closing time: 09:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን 3፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-04-28 10:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Debay Telat Gen Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Published: Apr 13, 2026
  • Posted at: 2026-04-15T11:50:22.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders