የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችና ጫማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04/2018
የዲላ ትምህርት ኮሌጅ
ሀ/ የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችን ማለትም
1. የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችና ጫማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት ከላይ የተጠቀሱ የተዘጋጁ የደንብ ልብሶችንና ጫማዎችን ዋጋ ቫትን አካቶ በመሙላት ኮሌጁ ለዚሁ ሥራ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለ/ በዚሁ መሰረት
1/ በጨረታው የሚሣተፉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር አጠናቅቀው የከፈሉ ፣ የምዝገባ የምሰክር ወረቀት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
2/ ተጫራቾች በ(VAT) ከፋይነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፣
3/ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሣብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችሉም፤
4/ የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣
5/ ተጫራቾች በጨረታው ለሚሣተፉባቸው ዕቃዎች ካቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ከላይ የተገለጸውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 11,000.00 /አስራ አንድ ሺህ / በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6/ ተጫራቾች በጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሳተፍ ይችላሉ፣
7/ ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፣
8/ የተዘጋጀ የደንብ ልብስና ጫማ በሳምፕል መልክ ማቅረብ ይኖርበታል።
9/ የቀረበው የተዘጋጀ የደንብ ልብስና ጫማ ሳምፕል ጨረታው ተከፍቶ ከመታየቱ በፊት ስለትክክለኛነቱ በባለሙያ ታይቶ ትክክለኛ ያልሆነ ሳምፕል ያቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይደረጋል።
10/ ኮሌጁ በጨረታው አሸናፊ ለሆነው ድርጅት ክፍያ የሚፈጽመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው።
11/ ተጫራቹ ለጨረታው የሚያቀርቧቸውን ሠነዶች ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናቸውን በሚገባ በታሸገ ኤንቨሎኘ ውስጥ በማሸግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ የዲላ ትምህርት ኮሌጅ የግልጽ ጨረታ ቁጥር 04/2018 ዓ/ም በማለት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
12/ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይቆያል። ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመሥሪያ ቤቱ የማኔጅመንት መሰብሰቢያ አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል።
13/ የጨረታው አሸናፊ ድርጅት በጨረታው ያሽነፈባቸውን እቃዎች ማንኛውም ወጪ የጉምሩክ ቀረጥን ጨምሮ በመሸፈን ዕቃዎቹን የሚያስረክበው ዲላ ትም/ ኮሌጅ ነው።
14/ ተጫራቾች ለጨረታ በሠነድ ላይ ያቀረቡት ዋጋ ያሸነፋባቸውን የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች እስከሚያስረክቡበት ጊዜ ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
15/ ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ መሆናቸው ከተረጋገጠ በኋላ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በማስያዝ ከመሥሪያ ቤቱ ጋርየሽያጭ እና የግዥ ውል ይፈራረማሉ።
16/ የቀረበው የተዘጋጀ የደንብ ልብስና ጫማ ሳምፕል ጨረታው ተከፍቶ ከመታየቱ በፊት ስለትክክለኛነቱ በባለሙያ ታይቶ ትክክለኛ ያልሆነ የተዘጋጀ የደንብ ልብስና ጫማ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይደረጋል።
17/ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ የዕቃዎቹን አይነት ፣ የአምራቹን ስም፤ የተመረተበትን ሀገር ፤ የሞዴል ቁጥርና የተመረተበትን ዓመት ጭምር ማካተት ይኖርበታል።
18/ አሸናፊው ድርጅት የተዘጋጀ የደንብ ልብስ የሚያቀርብ ስለሆነ የእያንዳንዱን ሠራተኛ ልብስ ልኬትና የጫማ ቁጥር እንዲሁም የሸሚዝ ቁጥር ቦታው ላይ በመገኘት ለክቶ የሚወስድ ይሆናል።
19/ የደንብ ልብሱ ከለር ለሥራ መደቦቹ ተስማሚ የሆነ ወጥ ከለር መሆን ይኖርበታል።
20/ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፣
21/ የጨረታ ሰነዱን ከዲላ ትምህርት ኮሌጅ ብር 100 በመክፈል ከግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር በግዥ ማግኘት ይችላሉ።
22/ መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ እንዲሁም ብዛት የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ
የዲላ ትምህርት ኮሌጅ ስ.ቁ 046-331-36-29
የዲላ ት/ኮ/ግ/ፋ/ን አስተዳደር ስ.ቁ 046-331-4251
ፋክስ 046-331-2492
የዲላ ትምህርት ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-04 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: Dilla Education College
- Bid bond: 11,000.00 /አስራ አንድ ሺህ /
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Apr 16, 2026
- Posted at: 2026-04-16T08:00:56.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.