በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ እቃዎች በግልፅ እንዲሁም በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 26/2018 ዓ.ም
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተለያየ ጊዜ ውርስ የተደረጉ አልባሳት፣ ጫማ ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ኮስሞቲክስ፣ የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ምግብ ነክ፣ Woven bag እና ተሽከርካሪ በግልፅ እንዲሁም ኮስሞቲክስ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ እና ጫማ በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን መስፈርቶቹ፡-
1) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ሲሆን ተሸከርካሪ መጫረት ለምትፈልጉ ንግድ ፈቃድ የማይጠይቅ በመሆኑ ማንኛውም እድሜው ከ-18-ዓመት በላይ የሆነ የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ግለሰብ መጫረት ይችላል።
2) በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የፀና የንግድ ፈቃድ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር መ/ቤት የሚሰጥ የምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል ግለሰብ መጫረት ይችላል።
3) የዚህ አንቀፅ ተራ ቁጥር (1) ድንጋጌ ቢኖርም ግምታዊ ዋጋው ከብር 2 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ሰርተፍኬት) ማቅረብ አያስፈልገውም።
4) በጨረታ የሚሸጠው እቃ በኮሚሽኑ ቁጥጥር ስር ከመግባቱ በፊት ባለቤት የነበረ ወይም የባለቤቱ ወኪል ወይም ቤተሰብ የሆነ ሰው በማንኛውም መልኩ በጨረታው መሳተፍ አይችልም።
5) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ አይነትና ብዛት የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) እየከፈሉ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው (6) ቀን 03፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
6) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታው የዕቃዎችን ዝርዝር በያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው ዓምድ ሥር የሚገዙበትን ዋጋ በአሀዝና በፊደል ገልፀው እና በተራ ቁጥር 1 ላይ የተገለፁትን በኢንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
7) የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ስድስተኛው ቀን በጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚካሄድ ሲሆን ግልፅ ጨረታዉ 3፡50 ሰዓት ተዘግቶ 4፡00 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ሀራጅ ጨረታው 4፡30 ሰዓት የሚጀመር ይሆናል።
8) ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ05 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመክፈል ንብረቶቹን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከፍለው የማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ተደርጎ እቃው እንደገና ለጨረታ ይቀርባል።
9) ተጫራቾች ለእቃዎች በሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ አሽናፊ ከሆኑ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ 15% (VAT) የሚጨመርበት ይሆናል።
10) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስተኛው ቀን ድረስ ለሽያጭ የተዘጋጁ እቃዎችን በኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ እና ስድስተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ።
11) ተጫራቾች ለግልፅ ጨረታ እቃዎች የሰጡትን የመግዣ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) እና ለሀራጅ ጨረታ የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብር በላይ ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር እንዲሁም የእቃው መነሻ ዋጋ ከ 2 ሚሊየን ብር በታች ለሆነ እቃ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000 (አንድ መቶ ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
12) መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ፡- 033 551 06 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-04-23
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-04-23 12:00
- Bid opening (note): በየሎቱ የተለያየ ነው
- Region: Amhara
- Publishing entity: Kombolcha Custom Branch Office
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published: Apr 17, 2026
- Posted at: 2026-04-17T07:38:53.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.