የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የተላለፉለትን በሕግ በመፍረስ ላይ ያለ የጥቁር አባይ ኮንስትራክሽን አ.ማ. ግቢ የሚገኙ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ልዩ ልዩ ንብረቶች ሽያጭ በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር LAMC/BD/06-08/2018
የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የተላለፉለትን በሕግ በመፍረስ ላይ ያለ የጥቁር አባይ ኮንስትራክሽን አ.ማ ግቢ የሚገኙ ልዩ ልዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ግሎባል በሚገኘው ከንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ጀርባ ባለው የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ በሚገኘው በፋይናንስ ኮርፖሬት ሰርቪስ መምሪያ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፤
2. ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ ሳሪስ ከንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው በሕግ በመፍረስ ላይ ያለ የጥቁር አባይ ኮንስትራክሽን ኢማ ግቢ ነው፡፡
3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ልዩ ልዩ ንብረቶች በተራ ቁጥር 2 ላይ በተጠቀሰው ቦታ አድራሻ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፤
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው ሚያዝያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሑድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፤
6. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፣
7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲ.ፒ.ኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው፡፡
8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ንብረቶቹን በ15 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፤
9.ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0942-52-36-99 / 0916-40-55-90 ወይም 0912-13-47-91 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፤
10. ኮርፖሬሽኑ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-01
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-05-01 11:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Liability and Asset Management Corporation
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Apr 17, 2026
- Posted at: 2026-04-17T08:23:03.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.