የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም ችግር ለመፍታት ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል ባለ 5 ወለል ከ12 ብሎክ በላይ በቂ የመኪና ማቆሚያ የ24 ሰዓት የውሃ እና መብራት አገልግሎት ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ በቂ የልጆች መጫወቻ ቦታ እና የጋራ መናፈሻ ቦታ ያላቸው ባለ ሁለት መኝታ የመኖ

Description

ለ2ተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ.ከ.አስተ.ገ.ጽ.ቤት 002/2018

የአዳማ ከተማ አስተዳደር በከተማ አስተዳደሩ በመኖሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የፍላጎትና የአቅርቦት አለመጣጣም ችግር ለመፍታት ወጪ ቆጣቢ ቤቶችን ገንብቶ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል ባለ 5 ወለል ከ12 ብሎክ በላይ በቂ የመኪና ማቆሚያ የ24 ሰዓት የውሃ እና መብራት አገልግሎት ለተለያዩ ዝግጅቶች የሚሆን የጋራ ቦታ በቂ የልጆች መጫወቻ ቦታ እና የጋራ መናፈሻ ቦታ ያላቸው ባለ ሁለት መኝታ የመኖሪያ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በካሬ የመነሻ ዋጋ በግልፅ ጨረታ መግዛት ለሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም የግል ወይም የመንግስት ድርጀት ወይም አክሲዮን ማህበር አወዳድሮ በሽያጭ ማስተላለፍ ይፈልጋል።

ስለሆነም ማንኛውም ለጨረታ የቀረቡ የመኖሪያ ቤቶችን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛዉም ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ግለሰብ ፡ የግል ድርጅት ወይም ለሰራተኞቻቸው መግዛት የሚፈልጉ የመንግሰት ወይም የግል ወይም የአክሲዮን ማህበራት ወይም ድርጅቶች ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ማታ 11፡30 ድረስ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሲንቄ ባንክ የአካውንት ቁጥር 1054551161211 በመክፈል ቦሌ ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ የጋራ መኖሪያ መንደር ህንጻ ቁጥር 10 በመቅረብ ደረሰኝ በመቁረጥ ቦሌ ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ የጋራ መኖሪያ መንደር ህንጻ ቁጥር 10 ግራውንድ ላይ ለዚሁ ተብሎ ከተከፈተው ቢሮ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።

ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በተጫራቾች መመሪያ ላይ በተገለጸው ፕሮግራም መሰረት ቦሌ ክፍለ ከተማ አንዶዴ ወረዳ የጋራ መኖሪያ መንደር ህንጻ ቁጥር 10 ፊት ለፊት በተዘጋጀው ቦታ ላይ ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በተከታዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል። መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በ 09 38 70  91 02 ይደውሉ

የአዳማ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-05-12
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ማታ 11፡30
  • Bid opening: 2026-05-13 09:00
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama City Finance and Economic Cooperative Bureau
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Apr 18, 2026
  • Posted at: 2026-04-18T08:06:06.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders