በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም
1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉት በሚመለከታቸዉ መስሪያ ቤቶች በአቅራቢነት የተመዘገቡና ለ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና በ eGP የተመዘገቡ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ ሥራዎች አገልግሎቶች፤ ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መወዳደር ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት (አስራ አምስት ቀናት) ከታች ከተጠቀሰው አድራሻ መግዛት ይችላሉ።
3. የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በማቅረብ መግዛት ይችላሉ። የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና ሥራ ሃደት ቢሮ ይሆናል፡፡
4 ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ : ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ ጨሪታ ተቀባይነት አይኖረውም ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለስለታል።
5. ጨረታው የሚከፈተው ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ሌሎች መገኘት የሚፈልጉ ባሉበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከቀኑ 4:30 የሚከፈት ይሆናል። 16ኛው ቀን የበአላት ቀን ከሆነ (የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና የ200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በታወቀ ባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
7. ርክብክብ የሚፈጸምበት ቦታ ወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳዳር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይሆናል።
8. የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
ለበለጠ መረጃ 046 180 0563 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00
- Bid opening: 2026-05-04 10:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30
- Region: South Ethiopia Regional State
- Publishing entity: የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ፕላን ልማት መምሪያ
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Apr 18, 2026
- Posted at: 2026-04-18T08:38:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.