የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ እና ለብዙ አመታት ያገለገሉ ንብረቶች እነሱም የተሽከርካሪ መሳሪያዎች፣ የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣ አላቂ ንብረቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ላፕቶፕ እና ፕሮጀክተር፣ ፕሪንተር እና የመሳሰሉት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጀቶች ባለስልጣን በተቋሙ ውስጥ የሚገኙ እና ለብዙ አመታት ያገለገሉ ንብረቶች እነሱም የተሸከርካሪ መሳሪያዎች፣ የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣አላቂ ንብረቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ላፕቶፕ እና ፕሮጀክተር፣ፕሪንተር እና የመሳሰሉት በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ ከተቋሙ ግዢና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት (15) ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን በአስራ ስድስተኛው ቀን ግን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን መሆኑን እናሳውቃለን።

2. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በሚል ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) የገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ) በማሰራት ከአዲስ አበባ ውጪ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡አሸናፊዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ጠቅላላ ዋጋ ከፍለው ሲመጡ ተመላሽ ይሆናል፤ለተሸነፉት ተጫራቾች የጨረታ ግምገማ ውጤት በጨረታ አፅዳቂ መፅደቁ ወይም ውድቅ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸ በኋላ ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።

3. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ 15 ቀናቶች ሆኖ በ16ኛው ቀን ጨረታው 4፡30 ተዘግቶ 5፡00 የሚከፈት ይሆናል።

4. ተጫራቾች ከድርጅቱ የግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ ክፍል ቢሮ ቁጥር 605 የንብረቶቹን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ 300/ሶስት መቶ ብር/ እየከፈሉ በመግዛት ከሰነዱ ላይ ሙሉ ዝርዝሩን ያገኛሉ።

5. የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ አዲስ አበባ ከተማ ቴዎድሮስ አደባባይ ከፍ ብሎ ህብረት ኢንሹራንስ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 808 በመገኘት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣

6. ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

7. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ንብረቶች የሚገኙበት ቦታ ቲዎድሮስ አደባባይ አካባቢ ህብረት ኢንሹራን ህንፃ 8ኛ ፎቅ ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 10፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፤

8. ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ለመግዛት ሲመጣ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000004664608 ሶስት መቶ ብር/300.00 በማስገባት የባንክ ደረሰኝ ይዞ መምጣት ይኖርበታል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፦ / 09-01-19-09-39 / 0913-95-20-41/ 09-11-89-44-13

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን


Tender details

  • Deadline: 2026-05-04
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡30
  • Bid opening: 2026-05-04 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ5፡00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Civil Society Organization Authority
  • Bid bond: 10%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Apr 18, 2026
  • Posted at: 2026-04-18T08:44:44.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders