ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት፣ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች አቅርቦት እና የዳታ፣ ቴሌ፣ ቲቪ፣ ሲሲቲቨ፣ ኦዲዮ እና ፋየር አላርም ሲስተም አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 42/2018፣43/2018 እና 44/2018
ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን እየገነባቸው ላሉት
1. ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የሳኒተሪ እቃዎች አቅርቦት ጨረታ ቁጥር 42/2018
2. ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እቃዎች አቅርቦት ጨረታ ቁጥር 43/2018
3. ለተለያዩ ፕሮጀክቶች አገልግሎት የሚውሉ የዳታ፣ቴሌ፣ቲቪ፣ሲሲቲቨ፣ኦዲዮ እና ፋየር አላርም ሲስተም አቅርቦት እና ገጠማ ስራ ጨረታ ቁጥር 44/2018 ግዥ ለመፈጸም ህጋዊና ብቃት ያላቸው ፋብሪካዎችና አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
1. በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ያላት፤
2. የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ቫትን ጨምሮ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፣
3. የጨረታ ሰነዱን ባ/ዳር ከተማ ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሃር አመልድ ህንፃ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ 7ኛ ፎቅ ለተጠቀሱት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ።
4. የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን / ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን (15 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር) ባህር ዳር ዋናው ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨራታ ሣጥኑ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ የተጠቀሱት የመክፈቻ እና የመዝጊያ ቀናቶች የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በእለቱ ቀን 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል።
1. የጨረታው ውድድሩ በሎት/በምድብ/ ድምር ዋጋ የሚታይ ሲሆን በአንድ ሎት/ምድብ ለተጠየቁ የስራ ዝርዝሮች ሙሉ በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት።
2. በጨረታ የተሞላወው ዋጋ የጨረታ ሠነዱ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ45 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
3. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ
ስልክ ቁጥር ባህዳር - 058-218-0538 / 09-18-01-06-17 / 09-18-71-66-16 / 09-98-18-71-78
አዲስ አበባ ፡- ስልክ ቁጥር 0111 265 338 / 09-18-80-03-64 / 09-11-90-86-29
የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-05-04
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-05-04 14:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሰነድ
- Published: Apr 18, 2026
- Posted at: 2026-04-18T08:48:23.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.