ኖህ ትራንስፖርት እና ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማህበር የድርጅታችን የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት) የሚሠራ የውጭ ኦዲተር አወዳድሮ ለ3 ዓመት ከ2018 ዓ.ም እስከ 2020 ዓ.ም ውል ተዋወሎ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የውጭ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ኖህ ትራንስፖርት እና ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማህበር የድርጅታችን የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት) የሚሠራ የውጭ ኦዲተር አወዳደሮ ለ3 ዓመት ከ2018 ዓ.ም እስከ 2020 ዓ.ም ውል ተዋወሎ ማሠራት ይፈልጋል።

ድርጅታችን ኖህ ትራንስፖርትና ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማህበር የተሰማራበት የንግድ ሥራ በደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት እና በአነስተኛ ሱቆችና መጋዘን በማከራየት የንግድ ሥራ ዘርፍ የተሰማራ ድርጅት ነው።

የሥራው ዝርዝር ተግባራት

1- የድርጅቱ የሒሳብ ምርመራ በአለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው ሪፖርት እስታንዳርድ መሰረት በጥራትና በተገቢው መንገድ ምርመራ በማድረግ የምርመራውን ሪፖርት በቅድሚያ የሪፖርቱን ድራፍት ረቂቅ ለማሳወቅና በሪፖርት ስምምነት ላይ ስንደርስ የመጨረሻውን ኦዲት ሪፖርቱ በ3 ዋና ትጅ ያቀርባል።

2- አክሲዮን ማህበሩ የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ መደበኛ ስብሰባ በዓመት 1 ጊዜ በሚያካሂድበት ጊዜ ለጉባኤው የኦዲት ሪፖርት የሚያቀርብ፤

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች ፤

  • ቴክኒክና ፋይናንሻል ፕሮፖዛላችሁን በዝርዝር ማቅረብ
  • በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ ኦዲት ቦርድ የተሰጠ ፈቃድ ማቅረብ
  • በ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት የቲን እና የቫት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት።

ስለሆነም ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 የተሟላ ማስረጃ በመያዝ በአካል በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

አድራሻ፡- ኖህ ትራንስፖርትና ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማህበር ዋና መስሪያ ቤት ሳሪስ ሪየስ ኢንጅነሪንግ ወረድ ብሎ ከዩኒቨርሳል ቆዳ ፋብሪካ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0114 425 521 / 0911 371 048

ኖኅ ትራንስፖርት እና ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-04-30
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት
  • Bid opening: 2026-04-30 17:00
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Noah Transport Share Company
  • Buyer address: ኖህ ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር ዋናው መሥሪያ ቤት ሣሪስ ክሪስ ኢንጅነሪንግ ወረድ ብሎ ከዩኒቨርሳል ቆዳ ፋብሪካ ፊት ለፊት
  • Published: Apr 20, 2026
  • Posted at: 2026-04-21T07:49:51.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders