በድጋሚ የወጣ የመኪና የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Description
በድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ለይላት ብርሀኑ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አብድልቃድር ዲኖ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/150239 በጥቅምት 9 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ እና በኮ/መ/ቁ/168850 በ12/9/2017 ዓ.ም በ20/02/2018 ዓ.ም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ/336979 በሐምሌ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ ቆሞ የሚገኝ የሠ/ቁ/ኮድ 3-B54872 አ/አ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 2,200,000 (ሁለት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መጋቢት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል፡፡ ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ 168850 በቀን 24/07/2018 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት 1/4ኛ 550,000 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ሆኖ የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የስራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ አፈ/ጽ/ቤት ስም C.PO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-05-15
- Bid closing time: 11:30
- Bid opening: 2026-05-15 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Federal Courts Judgement Execution Directorate
- Bid bond: 25%
- Published: Apr 20, 2026
- Posted at: 2026-04-21T07:54:06.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.